ወይ ሰው መሆኔ
ወይ ሕያው መሆኔ
ከወደድከው ጥሩ
ባትወድም ግን ዳሩ
ከወደድከው ጥሩ
ባትወድም ግን ዳሩ
ጠቆረም ነጣ ጣፈጠም መረረህ
በሁለት እግር ሁለት ዛፍ ነው ያማረህ
ከሄዋን መሆን ወይ ሉሲን መያዝ ነው
በአንድ ልብ ሁለት ለየቅል መውደድ ምንድነው
ወይ ሰው መሆኔ
ወይ ሕያው መሆኔ
የሰው ለየቅል መመኘት አያልቅ በእምነት በሃሳቡ
ንጉሥ ነህ የዓለም ያለውን መጽሐፉን በእጁ አንግቦ
ያው በዘፍጥረት በመጽሐፍ አምናለሁ ይላል
መልሶ ለርሱ ያዜማል በቋንቋ በዘሩ ይኮራል ይገርማል!
ጠቆረም ነጣ ጣፈጠም መረረህ
በሁለት እግር ሁለት ዛፍ ነው ያማረህ
ከአደም መሆን ወይ ደግሞ ከዓለም ነው
ዘር ለአደም የሰው ለዓለም የአባትህ ነው
ከወደድከው ጥሩ
ባትወድም ግን ዳሩ
ጠቆረም ነጣ ጣፈጠም መረረህ
በሁለት እግር ሁለት ዛፍ ነው ያማረህ
ከሄዋን መሆን ወይ ሉሲን መያዝ ነው
በአንድ ልብ ሁለት ለየቅል መውደድ ምንድነው
ኖሮም በምድር የሰው ልጅ መንገዱን መርጦ
መነሳት መውደቅ አይተውም መች ከአንዱ ረግቶ
ልኬትም ወዶ ጎኑ በእንቅልፍ ረግቷል
እደርሳለሁ ቢልም እግሩ መሄድ ታክቶታል ተምታቷል
ጠቆረም ነጣ ጣፈጠም መረረህ
በሁለት እግር ሁለት ዛፍ ነው ያማረህ
ከሄዋን መሆን ወይ ሉሲን መያዝ ነው
በአንድ ልብ ሁለት ለየቅል መውደድ ምንድነው
ወይ ሰው መሆኔ
ወይ ሕያው መሆኔ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist