ታሪክ ባላቅም ታሪክ ልስራና ታሪክ ይናገር
የሃሳቤን ፍሬ ታሪክ ይዞት ድንበር ይሻገር
እያደሩ ጥሬ በዝቷል ባለንበትም ሀገር
ማነው ባላገር "ባላገር!" ከማለት የሚሻገር
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ
ማነው ይሄ ባላገር? የዘመኔ ወጣቱ?
ሌላው በጠቆምው ላይ የሚጠቁመው ጣቱን?
አፍስሶ ድንጋይ ለይ ውሃ የሚፈልግ እሳቱን?
አይደበቅ ነገር ሀገሩን ትቶ ውጪ መሻቱ
አዎ የኔ ትውልድ ንቁ ነው ለውጥንም ፈላጊ
ግን ለውጥ ያለው በውስጣችን ነው አይደለም ተፈላጊ
ሀገር ትቶ የሚለወጥ አይለውጥም ሀገሩን
ታዲያ ማን ይሆን እሱ ማን ይሆን ባላገሩ
ማን ይሆን ባላገሩ ብዬ ስስል በአይነ-ህሊና
ትንሽ ባላገሮች ታዩኝ ባለሁበት ትልቅ ፊና
ፊናዬ ጥበብ ናት አዎ ተነዳች እንደ መኪና
መድረሻም ሳይሰጧት አዎ ነዷት ያለ ምንም ሚና
ፍለጋዬን በመቀጠል ፈርጁን ቀየርኩ ወደ ሌላ
ሌላው ባለበት ተቀምጧል እያለ ጎመን በጤና
ጤናን ግን ሲያጠነጥንው ገባው ጤና እንደጎደለው
እሱም ባላገር ካልሆነ ታዲያ ባለገሩ ማንው ቆይ
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ ማነው ባለ ሀገሩ ማን?
ባለ ሀገሩ
ባለ ሀገር መሆን ነው ባላገርነት ማለት
ግን አስመሰልነው ዘበት ስናወጋው ከአንደበት
በአንድነት ባላገር ነን ብንልስ ቆይ ምን አለበት
ምን አለ ያበጀ ትርጉም ሰተን በተፋየድንበት
ላገሩ የሰራ ሁሉ "እለዋለው ባላገሩ"
ባገሩ የኮራ ሁሉ "እለዋለው ባላገሩ"
ሀገሩም ለሱ ሀገሩ እሱም ለሷ ባላገሩ
አሁን የባላገር ትርጉም ያበቃል ማከራከሩ
የዘመኔም ወጣት ስማ በፊናውም ያልህ ሁሉ
ባላገር ትርጉሙ ጥሩ ነውና ባላገር በሉ
ባላገርም ስትባሉ በባላገርነት ኩሩ
ለሀገሩ ሰርቶ ሚኮራ ሁሉም ባለሃገር ነው
ስለዚህ ስሩ ሰርስሩ ወንድሞችንም ደጉሙ
መቆም ላቃተው ወዳጃችሁም ጠንክራችሁ ቁሙ
ታሪክ ብዬ እንደጀመርኩ ታሪክ መሆንን አልሙ
ባለሀገርን አንድ ቀን ታሪክ ያነሳዋል ስሙን
እሱ ነው
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
እሱ ነው
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
ባለሀገሩ ባለ ባለሀገሩ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist