Kishore Kumar Hits

eyob mekonnen - Wede Enate Bet lyrics

Artist: eyob mekonnen

album: Erotalehu


እንደው ሙሉ ሆኜ ተፈጥሬ
በቀቢፀ ተስፋ ታጥሬ
ያጣዉ የሌለኝ ደርሶ ቢመስለኝ
አወይ እግሬ
አወይ እግሬ
ወስዶ አወጣኝ ከሀገሬ
ንፁህ ፍቅር እምነት ሰላም ሳይጠፋ
ነገን የሚያኖር ተስፋ
ሁሉ ሞልቶ ሳለ ከሀገር መንደሬ
ስስት ከማታውቅ ምድሬ
ልቤ እሩቅ ተመኘ በሰማዉ ተረቶ
ንቆ የራሱን ትቶ
ያሉት ከንቱ ቢያየው ቀርቦ ቢረዳ
ሆነበት የህሊና እዳ ኡሁ
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለሁ
ወደ እናቴ ቤት በቃ እሄዳለሁ
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለሁ
ከአእዋፍ አፍ ወድቆ ተዘርቶ አብቦ
ሳያለፋ መብላት ጠግቦ
ሰፊ ውድ እርስቱን የአምላኩን ፀጋ
ክብሩን ነስቶት ዋጋ
ስደት ባዶ ቅዠት ወስዶኝ ከሃገሬ
ብስሉ ሊሆን ጥሬ
ለካስአያምርብኝ ደስታም ሃዘኔ
ያለሃገር ስኖር እ
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት በቃ እሄዳለው
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists