Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew Abreham - Be Miheretu lyrics

Artist: Dawit Getachew Abreham

album: Etebikihalew


ኃጥያተኛ ፡ ነበርኩ ፡ ዓለም ፡ ጉድ ፡ ያለልኝ
ለሰራሁት ፡ በደል ፡ ሞት ፡ የፈረዱብኝ
ገበናዬን ፡ ገልጠው ፡ እየገፈተሩኝ
ለፍርድ ፡ አቀረቡኝ ፡ በድንጋይ ፡ ሊወግሩኝ
ዳኛው ፡ ግን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ በእውነት ፡ አዘነልኝ
ውስጡን ፡ እያወቀ ፡ ለእኔ ፡ ፈረደልኝ
ከከሳሾቼ ፡ እጅ ፡ በጥበብ ፡ አስጥሎኝ
በእኔ ፡ ፋንታ ፡ እርሱ ፡ ሞቶ ፡ ከፈለልኝ
አዝ:- በምህረቱ ፡ ዛሬ ፡ ቆሜያለሁ
ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ
ነፍሴን ፡ ከሚሹ ፡ ከከሳሾቼ
ማምለጥ ፡ ችያለሁ ፡ ምህረት ፡ አግኝቼ
ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ
የምህረቱ ፡ ብዛት ፡ ከባሕር ፡ ይጠልቃል
ስለኀጢያተኛው ፡ በእውነት ፡ ግድ ፡ ይለዋል
እርሱ ፡ ነው ፡ ዳኛዬ ፡ የሆነኝ ፡ ጠበቃ
ቀድሞ ፡ የታደገኝ ፡ ሕይወቴ ፡ ሲያበቃ
ከሳሾቼ ፡ ሁሉ ፡ ድንጋያቸውን ፡ ጥለው
ወደ ፡ ኋላ ፡ ሸሹ ፡ ህሊና ፡ ወቅሷቸው
ስራዬን ፡ ሰርቶታል ፡ አሁን ፡ ነጻ ፡ ሰው ፡ ነኝ
ላዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እዘምራለሁኝ
አዝ:- በምህረቱ ፡ ዛሬ ፡ ቆሜያለሁ
ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ
ነፍሴን ፡ ከሚሹ ፡ ከከሳሾቼ
ማምለጥ ፡ ችያለሁ ፡ ምህረት ፡ አግኝቼ
ዋጋዬ ፡ ይሄ ፡ ነው
በእርሱ ፡ ደም ፡ ታጥቤያለሁ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ
ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ አድኖኛል
በእርሱ ፡ ቁስል ፡ ተፌውሻለሁ
ነፍሴን ፡ ከሚሹ ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ
አስመለጠኝ ፡ አኔን ፡ አዳነኝ
ዛሬ ፡ በደስታ ፡ ዘምራለሁ
በእርሱ ፡ ቁስል ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ
ፍቅሩን ፡ እያሰብኩ ፡ በፊቱ ፡ ዘምራለሁ
ከሞት ፡ አፍ ፡ ከጫፍ ፡ ላይ ፡ አውጥቶኛልና
ታሪኬን ፡ አወራለሁ
ምህረቱን ፡ እያሰብኩ ፡ በፊቱ ፡ ዘምራለሁ
ለነፍሴ ፡ መዳን ፡ ሆኖላታልና
ሥሙን ፡ እባርካለሁ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists