Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew Abreham - Tiz Yilegnal lyrics

Artist: Dawit Getachew Abreham

album: Etebikihalew


ትዝ ፡ ይለኛል ፡ የማልረሳው ፡ ብዙ ፡ ታሪክ ፡ አለኝ
ራሴን ፡ አውቃለሁ ፡ ማንነቴን ፡ ከየት ፡ እንዳነሳኝ
ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ሳስታውሰው ፡ ያለፈውን ፡ ሁሉ
ስታግዘኝ ፡ ያዩ ፡ ዓይኖቼ ፡ በእንባ ፡ ይሞላሉ
ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ

ቀን ፡ ይመሻል ፡ ደግሞ ፡ ይነጋል
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል
ትዝታውን ፡ ግን ፡ ለመርሳት ፡ ከቶ ፡ እንዴት ፡ ይቻላል
ባትደርስልኝ ፡ ባትዘረጋው ፡ የምህረት ፡ እጅህን
ሳስበው ፡ እፈራለሁ ፡ መጨረሻዬን
ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ
በደስታ ፡ በሀዘኔ ፡ ከቶ ፡ ሳትለየኝ

ተሸከምከኝ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ
ቀኖቹ ፡ ቢያልፉ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ

ዛሬ ፡ ቆሜ ፡ ዘምረዋለሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ብዙ ፡ ነው
አንዳች ፡ የለም ፡ ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው
አመሰግንሃለሁ
ሁሉም ፡ አልፎ ፡ ዛሬ ፡ ቆሜያለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እዚህ ፡ አለሁ
ስለነገ ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ
ሕይወቴ ፡ በእጅህ ፡ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists