Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew Abreham - Digis Azegajitwal lyrics

Artist: Dawit Getachew Abreham

album: Etebikihalew


ድግስ ፡ አዘጋጅቷል ፡ ንጉሡ ፡ በይፋ
ያላወቀ ፡ ሁሉ ፡ በከንቱ ፡ እንዳይለፋ
ለሚገባው ፡ ሁሉ ፡ በእውነተኛው ፡ በር
መንገዱ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር
ልብሳችንን ፡ አጥበን ፡ አጽድተን ፡ በደሙ
ተግተን ፡ እንጠብቀው ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ ሰዓቱ
አዝ:- አንድ ፡ ቀን ፡ አምላኬን ፡ እገናኘዋለሁ
ሚያየኝን ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ አየዋለሁ
በደስታ ፡ ሁሌ ፡ በፊቱ ፡ እዘምራለሁ
ዘለዓለም ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ
እንዴት ፡ ግሩም ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ጌታን ፡ የማይበት
ከዚህች ፡ ዓለም ፡ ስቃይ ፡ ከቶ ፡ የማርፍበት
ኢየሱስ ፡ ይመጣል ፡ ታጅቦ ፡ በክብር
አብረን ፡ እንሄዳለን ፡ ልንኖር ፡ ከእርሱ ፡ ጋር
አዝ:- አንድ ፡ ቀን ፡ አምላኬን ፡ እገናኘዋለሁ
ሚያየኝን ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ አየዋለሁ
ከደመና ፡ ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ እሄዳለው
ዘለዓለም ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ
እንዴት ፡ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ያን ፡ ቀን
አብረን ፡ እንሄዳለን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists