Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew Abreham - Ke Admas Bashager lyrics

Artist: Dawit Getachew Abreham

album: Etebikihalew


አድማስ ፡ ባሻገር ፡ ከዓይናችን ፡ የራቀ
ከሩቁ ፡ ስናየው ፡ ሰማዩ ፡ ወደቀ
ነገር ፡ ግን ፡ የአራቱም ፡ መጨረሻ ፡ አንተ ፡ ነህ
ፍጥረት ፡ እጅህ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ያህል ፡ ትልቅ ፡ ነህ
አዝ:- በእውነት ፡ እኛም ፡ አናውቅህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ከአእምሮአችን ፡ በላይ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ችሎታህ
ሥራዎችን ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወሩ
ይሁን ፡ ስትላቸው ፡ ሆኑ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ
ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን
ንፋስ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እንዴት ፡ ይበተናል
የበረዶው ፡ ክምር ፡ ማን ፡ አጥቦ ፡ አፅድቶታል
ምድርን ፡ ስትሰራ ፡ ማን ፡ ነበረ ፡ አብሮህ
እንዲህ ፡ አድርግ ፡ ብሎህ ፡ ማንስ ፡ አማከረህ
አዝ:- በእውነት ፡ እኛም ፡ አናውቅህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ከአእምሮአችን ፡ በላይ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ችሎታህ
ሥራዎችን ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወሩ
ይሁን ፡ ስትላቸው ፡ ሆኑ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ
ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን
ኪሩቤል ፡ ሱራፌል ፡ የሚያመሰግኑህ
እልፍ ፡ እእላፍ ፡ መላእክቶች ፡ ወድቀው ፡ የሚሰግዱልህ
በእውነት ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ (፪x)
አዝ:- በእውነት ፡ እኛም ፡ አናውቅህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ከአእምሮአችን ፡ በላይ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ችሎታህ
ሥራዎችን ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወሩ
ይሁን ፡ ስትላቸው ፡ ሆኑ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ
ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists