Kishore Kumar Hits

Bethlehem Wolde - Eregnaye lyrics

Artist: Bethlehem Wolde

album: Eregnaye


እረኛዬ አንተ የእኔ እረኛ
የነብሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ አሃሃ
እኮራለው ባንተ እመካለው
በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም
እረኛዬ አንተ የእኔ እረኛ
የነብሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ አሃሃ
እኮራለው ባንተ እመካለው
በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም
የነብሴ ንጉስ እየሱስ አንተ ለእኔ እረኛዬ ነህ
ነብሴን ከአዳኝ ወጥመድ ዘውትር ትጠብቀኛለህ
አንተ የእኔ እረኛ አተኛም አታንቀላፋም
በሰላም ውዬ አድራለው እኔ በምንም አልሰጋም
እረኛዬ አንተ የእኔ እረኛ
የነብሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ አሃሃ
እኮራለው ባንተ እመካለው
በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም
ካንተ ሌላ ወዳጅ ካንተ ሌላ እረኛ
ለኔስ ምንም የለኝ አንተ የማትተኛ
መልካም እረኛ የሱስ ስለኔ ነብሱን ሰቶኛል
ስላሙም ልቤን ሞልቶ በድል ያራምደኛል
እረኛዬ አንተ የእኔ እረኛ
የነብሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ አሃሃ
እኮራለው ባንተ እመካለው
በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም
በለመለመ መስክ ዘወትር ያሳድረኛል
በእረፍት ውሃ ዘንድ ጌታ እኔን ይመራኛል
ቸርነት ምርቱ እየተከተሉኝ
ከክፉ ይጠብቁኛል በድል ያራምዱኛል
እረኛዬ አንተ የእኔ እረኛ
የነብሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ አሃሃ
እኮራለው ባንተ እመካለው
በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም
ምድር ብትነዋወጥ ብትነዋወጥ
ሁሉም ነገር ስፍራውን ቢለቅ
ከቶ እንዳልፈራ ከቶ እንዳልናወጥ
ልቤን ሞላኸው በሰላም በረፍት
ምድር ብትነዋወጥ ብትነዋወጥ
ሁሉም ነገር ስፍራውን ቢለቅ
ከቶ እንዳልፈራ ከቶ እንዳልናወጥ
ልቤን ሞላኸው በሰላም በረፍት
ያረጋጋኸኝ በነውጡ አለም
ጋሻዬ ነህና ለዘለዓለም
እኔ ልበልህ እረድኤቴ
ስለሆንክልኝ አቅም ጉልበቴ
ያረጋጋኸኝ በነውጡ አለም
ጋሻዬ ነህና ለዘለዓለም
እኔ ልበልህ እረድኤቴ
ስለሆንክልኝ አቅም ጉልበቴ
እልሃለው እረዴቴ እልሃለው እረዴቴ እልሃለው እረዴቴ
እልሃለው እረዴቴ እልሃለው እረዴቴ እልሃለው እረዴቴ
እልሃለው እረዴቴ እልሃለው እረዴቴ እልሃለው እረዴቴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists