Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew - Fiker lyrics

Artist: Dawit Getachew

album: Amnihalehu


የእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር በምንስ ይገለፃል

አንድያ ልጁን ለሞት እስኪሰጠው ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዷል

ፍቅር እጅግ ግድ ብሎት ስለ ሀጢያተኛው ሞት

በደላችንን ሁሉ በልጁ ላይ አኖረ አምነን እንድንድንበት

ለጻድቅ ሰው የሚሞት በጭንቅ ይገኝ ይሆናል

ስለ ሀጢያተኛው ታዲያ ማንስ ግድ ይለዋል

እግዚአብሔር ግን ይወደዋል

ብዙ አስከፍሎታል የታላቅ ፍቅሩ ጥልቀት

ሀጢያት አረገው ልጁን ሀጢያት ማያውቀውን

እኛ የሱ ጽድቅ እንድንሆን

በምድር ሁሉ ላይ ጻድቅ ስለታጣ
የእግዚአብሔር ፀጋ ወደ ምድር መጣ
ወንድ ሴት አላለ ድሃ ወይም ሀብታም

በኢየሱስ ለሚያምን ኩነኔ የለበትም
ብርሃን በራ በጨለማ
የነፃነት ጩኸት ተሰማ

በሞት ጥላ ለነበሩ
ተከፈተ የምህረት በሩ
ብርሃን በራ በጨለማ
የነፃነት ጩኸት ተሰማ
በሞት ጥላ ለነበሩ
ተከፈተ የምህረት በሩ
(ፍቅር ነው ፍቅር እግዚአብሔር)
(ፍቅር ነው ፍቅር እግዚአብሔር)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists