Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew - Ante Melkam Neh lyrics

Artist: Dawit Getachew

album: Amnihalehu


ለአፍታ እልፍ ብዬ አሰብኩ የኋላዬን
አቤት ቸርነትህ ከስንቱ ታደገኝ
ስወጣና ስወርድ ስወድቅ ስነሳ
ስንት ምህረት አየሁ ከቶ ማይረሳ
የአንተ መልካምነት ዙሪያዬን ከቦታል
እንደ አንተ ሚወደኝ ከወዴት ይገኛል
ምህረት ቸርነትህን ነፍሴ እያሰበች
በቀንም በማታ ትባርክሀለች
በሕይወቴ ያለፉ የማልዘነጋቸው
ብዙ ው... ለታ አለብኝ ቆጥሬ ማልዘልቀው
እንባዬን አብሰህ በደስታ ቀየርከው
ከቁስልም አልፈህ ጠባሳዬን ሻርከው
የአንተ መልካምነት ዙሪያዬን ከቦታል
እንደ አንተ ሚወደኝ ከወዴት ይገኛል
ምህረት ቸርነትህን ነፍሴ እያሰበች
በቀንም በማታ ትባርክሀለች
ቀናቶች ነበሩ ወዴት ነህ ያስባሉ (ወዴት ነህ ያስባሉ)
ትናንትን ረስቼ እንዴት እንዳስመለጥከኝ (እንዴት እንዳስመለጥከኝ)
ግን ቆም ብዬ ሀሳብህን ሳስተውለው
እግዚአብሔር ለኔ ያለህ በጎና መልካም ብቻ ነው
አንተ መልካም ነህ አንተ መልካም
መልካም ብቻ ነህ ለዘላለም
(መልካም ነህ መልካም ነህ) እግዚአብሔር (መልካም ነህ)
(መልካም ነህ) ቢገባኝም (መልካም ነህ) ባይገባኝም (መልካም ነህ)
መልካም ብቻ ነህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists