Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew - Amelkihalehu lyrics

Artist: Dawit Getachew

album: Amnihalehu


አንተ ከቶ የማታውቀው በሂወቴ ምን አለ
ገና ሳልነግርህ ይገባህ የለ የልቤ እንዳለ
ስለዚህ ጥያቄዬን ገትቼ ላምልክህ ላክብርህ
ነውና የዘውትር ስራዬ መቀደስ ስምህን

እንዲህ እንዲያ እያልኩ ጊዜዬን አልፈጅም
አንተን ከፍ ሳደርግ ያንስብኛል ሁሉም
የመኖሬ አላማ ለአንተ ክብር ነው
ዘላለም ማምለኬን ሁኔታ አይቀይረው
ጌታ ከቶ የማታውቀው በሂወቴ ምን አለ
ገና ሳልነግርህ ይገባህ የለ የልቤ እንዳለ
ስለዚህ ጥያቄዬን ገትቼ ላምልክህ ላክብርህ
ነውና የዘውትር ስራዬ መወደስ ስምህን

አንተ እኮ ትልቅ ነህ ከነገሮች በላይ
ከአፍህ በወጣው ቃል ፍጥረት ፀንቶ የለም ወይ
ሁኔታ ያልቃኘው አምልኮና ክብር
እሰዋለው ዘውትር ላንተ ለእግዚአብሔር
እጆቼን ከፍ አድርጌ ስምህን እባርካለው
የሚገባህን ሁሉ ይዤ በፊትህ እቀርባለው
በእውነትና በመንፈስ
ነፍሴን በፊትህ ላፍስስ
ደስ ያሰኝህ መስዋቴ
ይሄ ነው የልብ መሻቴ
እግዚአብሔርነትህን አመልካለሁ
ክብርህን እያየሁ አመልካለሁ
ከሁኔታ በላይ አመልካለሁ
ፊትህን እያየሁ አመልካለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists