Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew - Ye Eyesus Menged lyrics

Artist: Dawit Getachew

album: Amnihalehu


በዚህች ምድር ስኖር ብርቱ ሰልፍ ቢኖርም
ንፋስ ማዕበሉ ሊጥሉኝ ቢጥሩም
እምነቴን ሊፈትን ዙሪያዩን ቢዞርም
የጠራኝ ክርስቶስ ስለኔ አሸንፎአል ሁሉንም
እሮጣለሁ ይሄን የጽድቅ ጎዳና
እሮጣለሁ ይሄን የህይወት መንገድ
ወስኛለው መስቀሉን እያየሁ ልሄድ
ከኢየሱስ ሌላ ላልወድ
ወደ ኋላም ከቶ ላልሄድ
ግብ ግብ ከኔ ጋር ብዙ ቢያዝለኝም
ነፍስን በሚያደክም ትግል ውስጥ ብኖርም
ስጋዩን እየጎሸምኩ ወደ ፊት እሔዳለሁ
የምኖርለትን አላማ እያየሁ
እሮጣለሁ ይሄን የጽድቅ ጎዳና
እሮጣለሁ ይሄን የህይወት መንገድ
ወስኛለው መስቀሉን እያየሁ ልሄድ
ከኢየሱስ ሌላ ላልወድ
ወደ ኋላም ከቶ ላልሄድ
በፀጋው ጉልበት እታመናለሁ
ብወድቅም እንኳን ዳግም እቆማለሁ
ግን እስከ ፍፃሜ መስቀሉን እያየሁ
የኢየሱስን መንገድ እኖረዋለሁ
ኢየሱስን ነው አይኔ የሚያየው
ኢየሱስን ነው ተስፋ የማደርገው
መስቀሉን ብቻ ነው ትኩር ብዩ የማየው
እስከፍጻሜ ለክብር እሮጣለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists