Dawit Getachew - Ante Bicha lyrics
Artist:
Dawit Getachew
album: Amnihalehu
ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ
ለክብርህ አህዛብ ቢሰለፍ
አይበዛብህም ቢዘመርልህ
አያንስብህም ባንሰዋልህ
አንተ ያው እግዚአብሔር ነህ
የሚመስልህ የሌለህ
ለዘላለምም ጸንተሀል
ካንተ በላይስ ክብር የታል
አንተ ብቻ እግዚአብሔር
በዙፋንህ ጸንተህ የምትኖር
ታላቅ አምላክ ነህና
ክንድህ የጸና
ሁሉን በቃልህ ፈጠርክ
በእስትንፋስህ ምድርን ሞላህ
የሚመስልህ የሌለህ
ድንቅ አምላክ ነህ
♪
ሐያላን የታሉ
አንተ ላይ የተማማሉ
ተረት ሆነ ታሪካቸው
እስትንፋስህ በተናቸው
አንተ ግን በክብርህ
እስካሁን እንዳማረብህ
ታላቅ ክንድህም አልደከመም
ታምር ይስራል ለዘለዓለም
አንተ ብቻ እግዚአብሔር
በዙፋንህ ጸንተህ የምትኖር
ሀያል አምላክ ነህና
ክንድህ የጸና
ሁሉን በቃልህ ፈጠርክ
በእስትንፋስህ ምድርን ሞላህ
የሚመስልህ የሌለህ
ድንቅ አምላክ ነህ
ከፍጥረት ጋራ አብሬ
አቀርባለሁ ዝማሬ
ባይመጥንህም እንኳን
ታላቅ ክብር
ዝም ከማለት ይልቅ
መጥቻለው ላደንቅህ
ታላቅነትህን እያየሁ
ዘምራለሁ
♪
ሀያል ነህ ሀያል 2 x
እግዚአብሔር ሀያል ነህ
ክንድህ ሀያል ነው
ሀያል ነህ ሀያል 2 x
በቻህን ሀያል
ብርቱ ነህ ብርቱ 2 x
እግዚአብሔር ብርቱ ነህ
ብርቱ ነህ ብርቱ 4x
ሕያው ነህ ሕያው 2 x
እግዚአብሔር ሕያው ነህ
ሕያው ነህ ሕያው 2 x
ያለህ የነበርክ ሕያው
ደግሞም የምትነግስ ንጉስ
ንጉስ ነህ ንጉስ ነህ 3 x
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist