Dawit Getachew - Efeligihalew lyrics
Artist:
Dawit Getachew
album: Amnihalehu
አንተ የልቤ ረሀብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት ከምትገኝበት
በመቅደስህ ሆነህ ሁሌ አስብሃለሁ
ደስ የሚያሰኘውን ፊትህን እሻለሁ እፈልግሀለው
እንደምትናፍቅ ዋላ ወደ ውሃ
አግኝታ እስክትረካም ከዛ በበረሀ
ምንም አይታያት ማንም አያስቆማት
እንዲሁ አምላኬ ነው የነፍሴ ጥማት
ነው የነፍሴ ጥማት
አገኘሁህ እና ጥሜን አረካኸው
ግን ደሞ እርካታዬ አንተን ሚያስናፍቅ ነው
አሁንም አሁንም ልቤ ይፈልግሃል
በነገሮች መሀል ሀሳቤ ይወሰዳል ወደአንተ ይሄዳል
አንተ የልቤ ረሀብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት ከምትገኝበት
ዋና የልቤ ትኩረት የአይኔ ደግሞ ፍዘት
የጆሮዬ ጉጉት ድምፅህን ለመስማት
በእጅህ ለመነካት
♪
ረሀቤ ክብርህ ነው ውበትህ ጥማቴ
በሰማዩ ስርዓት ተወስዷል መሻቴ
የምድርን ግሳንግስ ትቼ ወደኋላ
ወዳንተ እሮጣለው ዘወትር እንድሞላ ረሀቤ እንዲሞላ
አንተ የልቤ ረሀብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት ከምትገኝበት
ዋና የልቤ ትኩረት የአይኔ ደግሞ ፍዘት
የጆሮዬ ጉጉት ድምፅህን ለመስማት
በእጅህ ለመነካት
♪
በየእለቱ ሙላኝ ልቤንም ለውጠው
በእየሱስ የነበረውን ሀሳብ በእኔም ደግሞ ሙላው
በትላንቱ ሙላት ትዝታ መኖር አልፈልግም
ዛሬም ትሻለች ነፍሴ እንደአዲስ ከቶ አልለምድህም
እፈልግሃለው እፈልግሃለው
በሙሉ ልቤ አንተን እሻለሁ
እፈልግሃለው እፈልግሃለው
በሙሉ ሃይሌ አንተን እሻለሁ
እፈልግሃለው እፈልግሃለው
በሙሉ ልቤ አንተን እሻለሁ
እፈልግሃለው እፈልግሃለው
በሙሉ ሃይሌ አንተን እሻለሁ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist