Dawit Getachew - Eyesus lyrics
Artist:
Dawit Getachew
album: Tariken Sera
ከፍጥረታት በፊት ኢየሱስ ነበረ
አለምም በሙሉ በእርሱ ተፈጠረ
የነበረ ያለ በክብር የሚኖር
አምላክ ነው እራሱ ያለ እንደ እግዚያብሔር
የእግዚያብሔር ደስታ ነው ውድ አንድ ልጁ
ወደ አብ መድረሻ ብቸኛ መንገዱ
የሕይወት ውኃ ነዉ የሚፈስ ዘላለም
ከእርሱ የሚጠጣ ዳግም አይጠማም
እነሆ ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ
ያለምን ሁሉ ሀጥያት በደሙ ሊያስወግድ
የባርያን መልክ ይዞ ሰውን ሆኖ መጣ
በእርሱ ላይ አረፈ የሀጥያታችን ቁጣ
ክብር ይሁን ለኢየሱስ
ክብር ይሁን ላዳነን
መንግስትና ካህናት ለእግዚአብሔር ልጆች ላረገን
የመማፀኛ ግንብ ማምለጫ መዳኛ
አሳልፎ የማይሰጥ እውነተኛ እረኛ
ሊቀካህን ነው ኢየሱስ የሚኖር ዘላለም
ከሱ ደም የሚያልፍ የሀጥያት ጉልበት የለም
እነሆ ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ
ያለምን ሁሉ ሀጥያት በደሙ ሊያስወግድ
የባርያን መልክ ይዞ ሰውን ሆኖ መጣ
በእርሱ ላይ አረፈ የሀጥያታችን ቁጣ
ክብር ይሁን ለኢየሱስ
ክብር ይሁን ላዳነን
መንግስትና ካህናት ለእግዚአብሔር ልጆች ያረገን
ላለውና ለነበረ በክብርም ለሚኖረው
ከሙታንም በኩር ሆኖ ሞትን ድላርጎ ለተነሳው
ለነገስታት ሁሉ ገዢ ሁሉን ቻይ አምላክ ለሆነው
ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ለኢየሱስ ክርስቶስ ነው
ክብር ይሁን ለኢየሱስ
ክብር ይሁን ላዳነን
መንግስትና ካህናት ለእግዚአብሔር ልጆች ያረገን
አአአአአአአአ አሜን
አአአአአአአአ አሜን
አአአአአአአአ አሜን
አአአአአአአአ አሜን
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist