Kishore Kumar Hits

Meskerem Getu - Ejochishen Zergi lyrics

Artist: Meskerem Getu

album: Ejochishen Zergi


ሃገሬ እምዬ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እማማ ሀገሬ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እናት ሀገር ምድር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ሰላም እፎይታሽን አድብቶ ሚናጠቅ
ክፉ ጨካኝ አውሬ ዳቢሎስ ደም አፋሶ ሚስቅ
ወንድም ከወንድሙ እያገፋተረ
በትውልዱ ልብ ውስጥ አመጻን ጥላቻን ያኖረ
ዛሬ በአምላክ ስልጣን ትዛዝ ከላይ ይውጣ
ጠላትሽ ይሰበር በጌታዬ ቁጣ
ዳር ድንበር ዙሪያሽን ይጠርሽ በእሳቱ
የጨለማው ምክር ይሁንበት ከንቱ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እማማ ሀገሬ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እናት ሀገር ምድር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
እናት እናት ሃገሬ እጆችሽን ዘርጊ እናት እናት ኢትዮጵያ
በምስራቅ በደቡብ በምራብ በሰሜኑ
ልጆችሽ ጥላቻን አዋድቀው በህብረት ያብሩ
በህዝብሽ ላይ ይታይ ይቅርታ እውነቱ
በቂም እምቢ ብለው በአንድነት ለፍቅር ይዝመቱ
እውነት ባደባባይ ይታይ በከፍታ
የሀሰት ምስክር የሚሰማው ይጣ
እናቶች አባቶች ወጣት ልጆች ሁሉ
ከክፋት ሸፍተው ለእርቅ ያዘንብሉ
ሃገሬ እማማ
ሃገሬ እማማ
ሃገሬ እማማ
ሃገሬ እማማ
ሃገሬ እማማ
እናት ሀገሬ ነሽ አምላክ የባረከሽ
ተስፋ ያደረግነው መጣልን ማለዳ
ፍርዱ አልዘገየም ወረደ በቁጣ
የአምላክ ፍርዱ መጣ ወረደ በቁጣ
የአምላክ ፍርዱ መጣ ወረደ በቁጣ
ወረደ ወረደ ወረደ ወረደ
ያገሬ ልጆች ቀና በሉ
የደስታ ቀን ነው አትዘኑ
የጸለይነውን አጊንተናል
ለአስጨናቂአችን መርዶ ሆኗል ለቅሶ ሆኗል መርዶ ሆኗል
ሰላም ይፍሰስ ይብዛ እልልታ
ንጋት ሆኗል አልፏል ማታ
ለአማኑኤል ለንጉሱ
ለምስጋና ከበሮ አንሱ
አሃ አሃ አመስግኑ
ከበሮ አንሱ አመስግኑ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists