Meskerem Getu - Lemin lyrics
Artist:
Meskerem Getu
album: Mengistih Timta
ስንቱ ያልተገባውን ከፍታ ረግጧል
ያልዘራዉን መልካም አጭዶ ተዘልሏል
መንገዱ ተቃንቶለት
ተሳክቶለታል በሕይወቱ
ሳይለፋ ምንም ሳይደክም
ባይተጋም ሙሉ ነዉ ቤቱ
ግን ለፃድቁ ተከለከለ በጽድቅ የዘራዉንም አጣ
ሕይወቱ ከፋበት ተጨነቀ ያለ ኃጥያቱ ተቀጣ
አላልፍልህ አለዉ ጨለማ መንጋቱን እየናፈቀ
ጥሮ ግሮ አላተረፋም በኪሳራ ያለዉ አለቀ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን
ግን ለምን
ለምን
ለምን
♪
የኃይላቸዉ ጥንካሬ ብርታታቸዉ ሲበዛ
በምስኪኑ ሲሳለቁ ሲያሳዩት ጭንቅ አበሳ
አመፀኞች ከፍ ሲሉ ሳይደክሙ ሲከናወኑ
ተከታይ ሲበዛላቸዉ ፃዲቁን ግን ሲኮንኑ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን
ግን ለምን
ለምን
እግዚአብሔር ከቶ አይባልም ለምን
የሚሰራዉን ስለሚመዝን
ፍርድ የተዛባ ቢመስልም እንኳን
አላማ አለዉ የእርሱ ዝምታ
♪
ኃጥአን በድጥ ላይ ናቸዉ
ይፈጥናል ዉድቀታቸዉ
እግዚአብሄር ሲነሳ ከፊት ነዉ ጥፋታቸዉ
ለልበ ንጹሐን ግን ቀን ይወጣላቸዋል
የደረሰባቸዉን እግዚአብሔር ተመልክቷል
ፃድቅ ፃድቅ እግዚአብሔር ፃድቅ
እርሱ አይሳሳት ፃድቅ ነዉ ፃድቅ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist