Meskerem Getu - Fiker Neh lyrics
Artist:
Meskerem Getu
album: Mengistih Timta
የዘላለም አምላክ የትውልድ መጠጊያ
የፍጥረት መጋቢ ድጋፍ መሸሸጊያ
ልጅህን በመስጠት ፍቅርን የተገበርክ
ዓለሙን በሙሉ እንዲሁ የወደድክ
ፍቅር ነህ እግዚአብሔር
ይቅር ባይ የምትምር
እልፍ ነው ቸርነትህ
አይቆጠር ማጽናናትህ
ፍቅር ነህ እግዚአብሔር
ይቅር ባይ የምትምር
እልፍ ነው ቸርነትህ
አይነገር ማጽናናትህ
♪
ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ እያልኩ ባዜምልህ
ደግሞ በአዲስ ምሕረት ታስደንቀኛለህ
አምላኬ አምላኬ እልሃለው እጠራሃለው ደግሜ
ልዩ ነው አወዳደድህ ላዜምልህ ፊትህ ቆሜ
ምን ዓይነት ፍቅር ነህ
እንዴት ያለህ መሃሪ ነህ
ምን ዓይነት ፍቅር ነህ
እንዴት ያለህ ወዳጅ ነህ
የዘላለም አምላክ የትውልድ መጠጊያ
የፍጥረት መጋቢ ድጋፍ መሸሸጊያ
ልጅህን በመስጠት ፍቅርን የተገበርክ
ዓለሙን በሙሉ እንዲሁ የወደድክ
ፍቅር ነህ እግዚአብሔር
ይቅር ባይ የምትምር
እልፍ ነው ቸርነትህ
አይቆጠር ማጽናናትህ
ፍቅር ነህ እግዚአብሔር
ይቅር ባይ የምትምር
እልፍ ነው ቸርነትህ
አይነገር ማጽናናትህ
♪
የሕይወት ምንጭ ነህ ፍቅርን ለተጠማ
የምታለመልም ነፍስን የምታረካ
አውርቼ አውርቼ አልጠግብም አይገልጽህም ቃላቴ
ደግነትህን ብዘምር አልገልጸውም በዚህ አንደበቴ
♪
ምን ዓይነት ፍቅር ነህ
እንዴት ያለህ መሃሪ ነህ
ምን ዓይነት ፍቅር ነህ
እንዴት ያለህ ወዳጅ ነህ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist