Meskerem Getu - Ante Tesebek lyrics
Artist:
Meskerem Getu
album: Mengistih Timta
በእድሜ ጠዋት ልጅ ሳለው አግኝተህ
ተንከባክበህ ያዝከኝ በሚያስገርም ትግስትህ
እንዳገለግልህ እድሉን አገኘሁኝ
ስላንተ እንድናገር በህዝብህ ፊት አቆምከኝ
እኔ ልታከብረኝ ክብርህን ትተሀል ክብርህን ትተሀል
ከሰማይ ሰማያት ስለኔ ወርደሀል ስለኔ ወርደሀል
የማልጠቅም ስሆን ሰው አድርገኸኛል ልጅህ አርገኸኛል
በኔ ፈንታ ሞተህ አስገኝተኸኛል አስገኝተኸኛል
ውድዬ አንተ ክበረህ ታይ
ኧረ አንተ ከብረህ ታይ
አንተ ነግሰህ ታይ በኔ ላይ
አንተ ደምቀህ ታይ
♪
ከመሬት አንስተህ በከፍታ ስፍራ እግሮቼ ሲቆሙ
ጌትነትህ ይግነን ከፍ ከፍ ያድርጉህ ባንተ ይደመሙ
ዛሬ ቀን ከወጣ በህዝብህ ፊት ብቆም በኔ ላይ ብትሰራ
ሰዉ ሁሉ አንተን ይይህ በሀገር በምድሩ ስላንተ ይወራ
አንተ ተወራ ኧረ አንተ ተወራ
አንተ ከብረህ ታይ በእኔ ላይ አንተ ነግሰህ ታይ
ኧረ አንተ ተሰበክ አንተ ደምቀህ ታይ
♪
እኔ ልታከብረኝ ክብርህን ትተሀል ክብርህን ትተሀል
ከሰማይ ሰማያት ስለኔ ወርደሀል ስለኔ ወርደሀል
የማልጠቅም ስሆን ሰው አድርገኸኛል ልጅህ አርገኸኛል
በኔ ፈንታ ሞተህ አስገኝተኸኛል አስገኝተኸኛል
ውድዬ አንተ ክበር
ኧረ አንተ ንገሥ
አንተ ከብረህ ታይ በኔ ላይ
አንተ ደምቀህ ታይ
♪
በበደሌ ምክንያት የተፈረደብኝ ነበርኩኝ የወደኩ
ጌታዬ አነሳኸኝ ሀጥያቴ ተሽሮ በደምህ ታጠብኩኝ
ባይገባኝ እንኳን ለኔ የሆንከው ነገር ፍቅርን ገልጦልኛል
መርገሜን ወስደህልኝ ውዴ በኔ ፈንታ በአብ ፊት ታይተሀል
አንተ ተወራ
ኧረ እንተ ተሰበክ
አንተ ከብረህ ታይ በኔ ላይ
አንተ ነግሰህ ታይ
አንተ ጎልተህ ታይ
አንተ በርተህ ታይ
አንተ ደምቀህ ታይ በኔ ላይ
አንተ ጎልተህ ታይ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist