Kishore Kumar Hits

Meskerem Getu - Lemndin New Yemninorew lyrics

Artist: Meskerem Getu

album: Mengistih Timta


ሰው - ሰው የሆነበት የሚኖርበት ምክንያት ካልገባው
በአካል ኖረ እንጂ የነፍሱን ክፍተት በምን ሊሞላው
ኑሮን ለማሸነፍ ሮጦ ሮጦ ቢደርስ ከግቡ
ተሳካለት ቢባል ሃሳቡ ሞልቶ እንዲያው ለደንቡ
ግን ይሄ አይደለም የሕይወት ትርጉሙ
ከማግኘት ይበልጣል ለተፈለጉበት መገኘት በውሉ
ሃብትን ለማካበት ከመባዘን ይልቅ
ለምን እንደምንኖር በተጋን ለማወቅ
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ

እርካታ በገንዘብ በመብል መጠጥ ከተገደበ
በጉብዝናው ጊዜ የፈጠረውን ሰው ካላሰበ
ኋላ በእድሜው ምሽት እንዳይፀፀት ከአሁኑ ይንቃ
የተፈለገበትን ምክንያት ያግኝ ቀኑ ሳያበቃ
በምድር ላይ ያስገኘን በሰማያት ያለ
ዓላማ ሰጥቶናል የምንኖርበት ከቁስ በዘለለ
ሁሉም በየድርሻው በተሰጠው ስራ
ለመፈፀም ይሩጥ የአምላክን አደራ
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ
ሰው - ሰው የሆነበት የሚኖርበት ምክንያት ካልገባው
በአካል ኖረ እንጂ የነፍሱን ክፍተት በምን ሊሞላው
ኑሮን ለማሸነፍ ሮጦ ሮጦ ቢደርስ ከግቡ
ተሳካለት ቢባል ሃሳቡ ሞልቶ እንዲያው ለደንቡ
ግን ይሄ አይደለም የሕይወት ትርጉሙ
ከማግኘት ይበልጣል ለተፈለጉበት መገኘት በውሉ
ሃብትን ለማካበት ከመባዘን ይልቅ
ለምን እንደምንኖር በተጋን ለማወቅ
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists