Kishore Kumar Hits

Meskerem Getu - Mine Alegne lyrics

Artist: Meskerem Getu

album: Eketelehalehu


ምን አለኝ ምን አለኝ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንዳገለግልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንድዘምርልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እኔ ደካማ ነኝ ሸክም የከበደኝ
ኃጢአት የበዛብኝ በደለኛ እኮ ነኝ
አይደለም በአንተ ፊት የማልመች ለሰው
እኔን ለመምረጥህ ምክኒያቱ ምንድን ነው
ምን አለኝ ምን አለኝ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንዳገለግልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንድዘምርልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
ጌታ በድካሜ አንተ ከመረጥከኝ
ለክብርህ ምሰዋው ምዘምረው አለኝ
በውስጤ የሞላው ውዳሴ ነውና
ለአንተ ይሁንልህ የአፌ ምሥጋና
ምን አለኝ ምን አለኝ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንዳገለግልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንድዘምርልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
ኃያል ሆነህ ሳለህ ከሁሉ የምትበልጥ
የምድር ጠቢባንን ሲገባህ ልትመርጥ
አንተ ግን እኔን ጠርተኸኛል ምን አለኝ
ምን አለኝ ምን አለኝ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንዳገለግልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንድዘምርልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
ብዙዎች ኃያላን በምድር ላይ ያሉ
በክብር በዝና በሀብት የተሞሉ
ዓይኖችህ ወደ እኔ ያያሉ ምን አለኝ
ምን አለኝ ምን አለኝ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንዳገለግልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
እንድዘምርልህ የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ
በፊትህ እንድቆም የሚያደርገኝ እኔ ምን አለኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists