Meskerem Getu - Fikere lyrics
Artist:
Meskerem Getu
album: Eketelehalehu
ለእኔ ከላይ ከሰማይ ከላይ ከሰማይ
መሞት የሚገባኝ ነበርኩ መጣልኝ ሲሳይ
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም የለም
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ አንዳች የለም
♪
ከላይ ከሰማይ የባሪያን መልክ ይዞ
በእኔ በኃጢአተኛዋ በፍቅር ተይዞ
ካለሁበት አዘቅት ከሞት ሊያወጣኝ
እርሱ ዋጋ ከፍሎ ነጻ ነሽ አለኝ
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም የለም
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ አንዳች የለም
♪
በዚያ በጐልጐታ በቀራኒዮ ላይ
ከቶ መች አፈረ እርቃኑ ሲታይ
የህማም ሰው ሆነ ተመታ በደዌ
እርሱ ዋጋ ከፍሎ ይኸው ዳንኩኝ እኔ
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም የለም
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ አንዳች የለም
♪
ወርዱና ስፋቱ የማይለካው
ጥልቅ ነው ፍቅሩ ወሰን የሌለው
የልቤ አይወጣም ብዙ ቃል ደርድሬ
ሳመሰግን ብውል በመልካም ዝማሬ
ለእኔ ከላይ ከሰማይ ከላይ ከሰማይ
መሞት የሚገባኝ ነበርኩ መጣልኝ ሲሳይ
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም የለም
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ አንዳች የለም
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist