Kishore Kumar Hits

Meskerem Getu - Ayzoh lyrics

Artist: Meskerem Getu

album: Eketelehalehu


ነገን ነገን ስታይ ቢጨልምብህ
በተስፋ ተራመድ እራዕይ ይኑርህ
ነገን ነገን ስታይ የጨለምብህ
በተስፋ ተራመድ እራዕይ ያለህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
ሥራ ብታጣ ገንዘብ ቢጠፋ ቢጨልምብህ አይዞህ
ሚረዳህ አጥተህ ብቻህን ብትሆን ተስፋ ባይኖርህ አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
ሥራ ብታጣ ገንዘብ ቢጠፋ ቢጨልምብህ አይዞህ
ሚረዳህ አጥተህ ብቻህን ብትሆን ተስፋ ባይኖርህ አይዞህ

ራስህን ስታስብ ሚሰማህ እንዳነስህ
ከሁሉ የበታች የሆንክ የመሰለህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
ልዩ የሆነ ችሎታ አለህ ተነስ ተገለጥ አይዞህ
ከማንም አታንስ ይኸው ራስህም ብቃት እኮ አለህ አይዞህ

መስራት ማትችልበት ምንም ምክኒያት የለ
ጠንክረህ ብትሰራ ብዙ ታጭዳለህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
የረፈደብህ እየመሰልህ ትተክዛለህ አይዞህ
በዚህ ጉብዝናህ በሙሉ ኃይልህ መራመድ ጀምር አይዞህ

አንድ ቀን ያልፋል አንድ ቀን ያልፋል አንድ ቀን ያልፋል
የወደደ ያከበረ ያፈቀረ አምላክ አለህ አለህ
የወደደ ያፈቀረ ያከበረ አምላክ አለህ አለህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists