Meskerem Getu - Amanuel lyrics
Artist:
Meskerem Getu
album: Eketelehalehu
በለጋነት ልቤ ፍቅርህ አሸንፎኛል
ከአንተ የትም አልሄድም
አንተ ተመችተኸኛል
ቃላትም የማይገልጹት ሰማያዊ ደስታ
በህይወት መመስከር መገዛት ለጌታ
እኔ ለብቻዬ ስሆን ጌታን አውቀዋለሁ
የአባትነቱን ፍቅር ቀምሻለሁ
ጌታን አውቀዋለሁ
ጌታን አመልካለሁ
ለጌታ እገዛለሁ
ጌታን እወደዋለሁ
♪
ኢየሱሴ አንተን ምን ብዬ ልግለጽህ
ቃላቶች አነሱ በምን ልተርክህ
እስከ ዛሬ ማውቀው የሚደንቅ ነገር
እጅጉን ትንሽ ነው ከአንተ ሲወዳደር
አማኑኤል (አማኑኤል) አማኑኤል
አማኑኤል (ከእኔ ጋር ነው)
ከእኔ ጋር ነው
እግዚአብሔር
(እግዚአብሔር)
♪
አባት ለልጆቹ ሃይማኖት ያወርሳል
ልጅ የተማረውን ስርዓት ይፈጽማል
ግን የጌታን ፍቅር አላስተዋለውም
ሃይማኖቱን እንጂ ጌታን ከቶ አልተቀበለም
ጌታ የግል ነህ
ለሚሹህ ቅርብ ነህ
አንተ ትሻሃላለህ
አንተ ታዋጣለህ
አምላኬ ሆይ አንተን ተረድቼሀለሁ
በወረስኩት ሳይሆን በግሌ አውቅሃለሁ
ከቤትህ ርቄ ወዴት እሄዳለሁ
ፍቅርህ ማርኮኛል አንተን መርጫለሁ
አማኑኤል (አማኑኤል) አማኑኤል
አማኑኤል (ከእኔ ጋር ነው)
ከእኔ ጋር ነው
እግዚአብሔር
(እግዚአብሔር)
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist