Kishore Kumar Hits

Meskerem Getu - Tewelede Endegena lyrics

Artist: Meskerem Getu

album: Eketelehalehu


በሕይወት ጎዳና ተስፋ ቆርጦ ሞቱን ለሚጠብቀው
እርፍትን ፍለጋ ጠቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው

በእራስህ ኃይል እና ጉልበት ነፍስህን አታድንም
በያዝቀው ሀብት እና ንብረት እርካታን አታገኝም
ይልቅስ ቶሎ ብለህ ና ትምክህትን ተው እና
ኢየሱስ ጌታዬ ብለህ ተወለድ እንደገና
ያኔ ነው እርካታህ ያኔ ነው ፍፁም ደስታ
ያኔ ነው እርካታህ ያኔ ነው ፍፁም ደስታ
በሕይወት ጎዳና ተስፋ ቆርጦ ሞቱን ለሚጠብቀው
እርፍትን ፍለጋ ጠቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው

በመስቀል ላይ ጌታ ሲሞት እዳህን ተሸክሞ
ከኃጢአት ደዌ ሊአድንህ ስላንተ እሱ ቆስሎ
ኃጢያትን ደምስሶልሃል ንፁህ ደሙን አፍስሶ
ና ልጄ ናና ይልሃል ስራህንም ጨርሶ
ድምጹን ስማው ወዳጄ ተከፍቷል የምህረት ደጄ
ድምጹን ስማው ወዳጄ ተከፍቷል የምህረት ደጄ
በሕይወት ጎዳና ተስፋ ቆርጦ ሞቱን ለሚጠብቀው
እርፍትን ፍለጋ ጠቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው
ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው የሚአድነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists