Kishore Kumar Hits

Lily Kalkidan Tilahun - Ejig Yemimir lyrics

Artist: Lily Kalkidan Tilahun

album: Beyet Hager Newe Egziabher


ጻድቅ ነህ ጌታ ስራህ ትክክል
የማታደላ የማትበድል
ለታላቅነትህ ፍጻሜ የለው
አቤት ጌታ ሆይ ስራህ ድንቅ ነው
ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x)
ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x)
ደግሜ ደጋግሜ እባርክሃለሁ
ምሥጋና ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው
ማለዳ በምሥጋና አፌን እከፍታለሁ
ከአንደበቴ ፍሬ ለአንተው እነግራለሁ
ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x)
ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x)
ይናገራል
ይናገራል ኦሆሆ
ይናገራል (፬×)
እጅግ የሚምር የሚራራ
አምላክ ነውና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና
እጅግ የሚምር የሚራራ
አምላክ ነውና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና
እንኳንስ ምረኅኝ ቀርቶልኝ አበሳ (፪x)
እኒስ ምሥጋናዬን ሁልጊዜው አልረሳ (፪x)
ምህረትህ በእኔ ላይ ጠንክራለችና (፪x)
ኃይሌ ታድሶልኝ ቆምኩኝ እንደገና (፪x)
እጅግ የሚምር የሚራራ
አምላክ ነውና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና
የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና (፬x)
ማዳኑን አስታውቆ ጽድቁንም ገለጠ (፪x)
ከእኛ መተላለፍ ምህረቱ በለጠ (፪x)
በሞገሱ ጋሻ እየከለለን (፪x)
ከአዳነን በኋላ ምህረቱ ያዘን (፪x)
አንድ ላይ ተስማሙ እውነትና ምህረት (፪x)
መግባትም ተቻለን እግዚአብሔር ያሌበት (፪x)
ጻድቅ ፈራጅ ሲሆን እንከን ያለበት (፪x)
አልፈረደብኝም ምህረቱ አይሎበት (፪x)
እጅግ የሚምር የሚራራ
አምላክ ነውና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ
ይድረሰው ምሥጋና
የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና (፪x)
ጌታ እልሃለሁ አንተን አመልካለሁ (፪x)
አምላክ እልሃለሁኝ አንተን አመልካለሁ (፪x)
አንተን አመልካለሁ አንተን አመልካለሁ (፪x)
ይገባሃል የአንደበቴ ቃል
ይገባሃል የአፌ ምሥጋና
ይገባሃል ልዘምርልህ
ይገባሃል ላገለግልህ
እኔ አምላክ እልሃለሁኝ አንተን አመልካለሁ (፭x)
እስከዛሬ ተመስገን ብያለሁ ተባረክ ብያለሁ አሃ
ከፍ በል ብያለሁ እስከዛሬ ተመስገን ብያለሁ
ተባረክ ብያለሁ አሃ ከፍ በል ብያለሁ
ደግሞ ዛሬ ዛሬ ምን ልበል
ዛሬ ምን ልበል
ደግሞ አሁን አሁን ምን ልበል ጌታ
አሁን ምን ልበል
ደግሞ ዛሬ ዛሬ ምን ልበል
ዛሬ ምን ልበል ዛሬ ምን ልበል
ይገባሃል የአንደበቴ ቃል
ይገባሃል የአፌ ምሥጋና
ይገባሃል ላገለግልህ
ይገባሃል ልዘምርልህ
ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists