Kishore Kumar Hits

Agegnehu Yideg - Haylegna lyrics

Artist: Agegnehu Yideg

album: Haylegna Endante Yelem, Vol. 1


በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ
ማኅተሙን ሊፈቱ አንዳቸውም አልቻሉ
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ
አንተ ግን ሃሌሉያ
አንተ ግን ችለሃል ማኅተሙን ልትፈታ
ከባርነት አገር ወደ አንተ ያመጣኸን
ቀንበርን ሰባብረህ አርነት ያወጣኸን
በጨለማ ያለ ህዝብ ታላቅ ብርሃን አየ
ከሰቆቃ ኑሮ ከሴይጣን ተለየ
ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም
የሚጤሰውን ጧፍ አጥፍተህ አታውቅም
ለደካማው ኃይልን ለጭንጋፉ ሞገስ
ካፍ ባል ጌታዬ ለዘለዓለም ንገሥ
ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ
ማኅተሙን ሊፈቱ አንዳቸውም አልቻሉ
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ
አንተ ግን ችለሃል ማኅተሙን ልትፈታ
ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
ሞተሃል ተብሎ እኛም ተስፋ ቆርጠን
በራችንን ዘግተን አዝነን ተቀምጠን
አንተ ግን ልዩ ነህ ታሪክ ለውጠሃል
ሞትና መውጊያውን ለዘለዓለም ሰብረሃል
ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
ትዕቢተኛውን ፈርዖን ሊያጠፋን ሲነሳ
ዙሪያችንን ሲዞር ሊውጠን እንደ አንበሳ
ቀድመህ ደረስክና አፉን ለጐምክልን
ምን እንበላ ሌላ ለእኛስ ዘለዓለም ንገሥልን
ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ
አንዳቴ የላም ንጋስ ዘላለም
አንዳቴ የላም ንጋስ ዘላለም
አንዳቴ የላም ንጋስ ዘላለም
ኦው አምላክ አንዳቴ የላም ንጋስ ዘላለም
ኦው አምላክ አንዳቴ የላም ንጋስ ዘላለም
ንጋስ ዘላለም አያሱስ ንጋስ ዘላለም
ክባር ዘላለም አያሱስ ክባር ዘላለም አያሱስ
ግዛን ዘላለም አያሱስ ግዛን ዘላለም አያሱስ
ግዛን ዘላለም አያሱስ ግዛን ዘላለም አያሱስ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists