Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Yayihal lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
በምድረ ፡ በዳ ፡ ያለኸው
እንደ ፡ አጋር ፡ ያነባኸው
የሚያይህንስ ፡ ብታየው
ፍጻሜህማ ፡ ተስፋ ፡ አለው
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ኑሮ ፡ ቢመሳቀልብህ
የያዝኸው ፡ ቢበተንብህ
ጌታም ፡ የተወህ ፡ ሲመስልህ
ጠላትህ ፡ ሲዘብትብህ
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ልብህ ፡ ሲያዝን ፡ ሲተክዝ
ለሕይወትህ ፡ ጽኑ ፡ ምርኩዝ
አይዞህ ፡ ባይ ፡ የሚያበረታ
ከቶ ፡ ማን ፡ አለ ፡ እንደ ፡ ጌታ?
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ሸክምን ፡ የሚያራግፍ ፡ ጌታ
የችግረኞች ፡ መከታ
ታማኝ ፡ የበጐች ፡ እረኛ
አማኑኤል ፡ አለን ፡ ለእኛ
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ያይሻል፣ ኢየሱስ ፡ ያይሻል
ያይሻል ፣ ባርግጥ ፣ ያይሻል
ያንቺ ፣ ናገር ፣ ይጋዳዋል
ልታዳግሺም ፣ ይማጣል
ያያናል ፣ አያሱስ ፣ ያያናል
ያያናል ፣ በዕውነት ፣ ያያናል
ያኛም ፣ናገር ፣ ይጋዳዋል
ልታዳጋንም ፣ ይማጣል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists