Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Beza Yehonkilign lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


ርዕስ፡ቤዛ የሆንክልኝ
ዘማሪ፡ተስፋዬ ጋቢሶ
በወርቅ ይሁን በብር በጥበብ በዕውቀት
የዳነ ማን አለ ከኃጢአት ውድቀት
ጌታ ሆይ አንተ ነህ ጽድቅን ያለበስኸኝ
በምሕረት አማልደህ ከአብ ያስታረቅኸኝ
ቤዛ የሆንክልኝ ኢየሱስ ጌታዬ
የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ
ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን
ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን
በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ሥራ
ከዘለዓለም ሞት ዳንኩኝ ከመከራ
በነጻ ታድዬ የጽድቅን ሥጦታ
ምሥጋና እሰዋለሁ ለተቤዠኝ ጌታ
ብላቴንነቴን ድካሜን ገምተህ
አንተ ብርቱ ጌታ በእኔ ላይ ተገልጠህ
የበረታብኝን ጠላቴን ቀጥቅጠህ
ድል ያጐናተጸፍኸኝ ኢየሱስ አንተ ነህ
መልካሙን ሥራህን በሕይወቴ ፈጽመህ
እንድትታይብኝ በኑሮዬ ጐልተህ
ይህ ነው ልመናዬ የዘወትር ጸሎቴ
ክብሬ ዕርካታዬ አንተ ነህ ትምክህቴ
Soli Deo Gloria music
#ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ#

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists