Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Abetu Gettachin lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


::አቤቱ ፡ ጌታችን፣ እስኪ ፡ እናመስግንህ
::ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ "ክበር" ፡ እንበልህ
::አቤቱ ፡ ጌታችን፣ እስኪ ፡ እናመስግንህ
::ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ "ክበር" ፡ እንበልህ
ሰይጣን: አንዴ: ሳንገል: ያባጣራሺ: አቱ
ዕምነት ፡ ተስፋችንን ፡ ሊያጨልም ፡ ዝቶ
አምርሮ ፡ ቢነሣም ፡ እጅግ ፡ ተቆጥቶ
ተገዝቶ ፡ አየነው ፡ በአንተ ፡ ድል ፡ ተነሥቶ
::ስለ ፡ ዕምነታችን ፣ ስለ ፡ ሕይወታችን
::የተሟገትክልን ፣ ተመስገን ፡ ጌታችን
የተጓዝንበትን ፡ መንገድ ፡ ሊያቋርጥ
ጠላታችን ፡ አልፎ፡ እንቅፋት ፡ ቢያስቀምጥ
የተመሸገውን ፡ ከፍ ፡ ያለውን ፡ ቅጥሩን
አፈራርሰህ ፡ ጣልከው ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን
::አንተ ፡ ቅን ፡ የሆነን፡ መንገድ ፡ ታቀናለህ
::የተዘጋውንም ፡ በር ፡ ትከፍትልናለህ
የሕዝብህን ፡ ስድብ ፡ ከምድር ፡ አስወግደህ
ከፊታቸውም ፡ ላይ ፡ እንባቸውን ፡ አብሰህ
ራሣቸውን ፡ በዘይት ፡ በሞገስ ፡ ቀብተህ
በምሥጋናቸውም ፡ አንተ ፡ ትነግሣለህ
::ለታናሹ ፡ መንጋ ፡ በዝቷል ፡ ቸርነትህ
::ክበር ፡ አምላካችን ፡ ዘላለም ፡ ልዑል ፡ ነህ
ግብዣን ፡ አዘጋጅተህ ፡ በክብር ፡ ጠራኸን
በንጉሥ ፡ ገበታ ፡ ይኸው ፡ አስቀመጥከን
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ በከበረው ፡ ሥፍራ
ነፍሣችን ፡ ጠገበች ፡ ከሕይወት ፡ እንጀራ
::ፈቅደን ፡ ከልባችን ፡ እናመልክሃለን
::ለዘለዓለሙም ፡ ለአንተ ፡ እንገዛለን
::ፈቅደን ፡ ከልባችን ፡ እናመልክሃለን
::ለዘለዓለሙም ፡ ለአንተ ፡ እንገዛለን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists