ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
::እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
::እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
::ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
::እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
::እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
::ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ
ማዕበሉ ፡ ሳይጥለኝ ፣ ውኃ ፡ ሳያሰጥመኝ
እጄን ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ወንዝ ፡ አሻገረኝ
የፈተናው ፡ እሣት ፡ ወላፈን ፡ ሳይጐዳኝ
በጌታዬ ፡ ፀጋ ፡ በሕይወት ፡ አለፍኩኝ
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
::እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
::እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
::ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ
ከሕያዋን ፡ ጋራ ፡ ኖሬ ፡ እንዳከብረው
ፈተናን ፡ አልፌ ፡ እንዳመሰግነው
ኢየሱስ ፡ ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ አበረታኝ
ከአንበሣው ፡ አፍም ፡ ደጋግሞ ፡ አወጣኝ
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
::እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
::እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
::ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ
ሕይወቴን ፡ ለአምላኬ ፡ አደራ ፡ እየሰጠሁ
በእረኝነቱ ፡ ሥር ፡ ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
በእርሱ ፡ ተጠብቄ ፡ አገሬ ፡ እገባለሁ
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
::እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
::እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
::ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ
ጌታ ፡ የሠራውን ፡ ድንቅ ፡ አስታውሳለሁ
ስላለፈው ፡ ዘመን ፡ አመሰግናለሁ
ከፊቴ ፡ ላለውም ፡ በእርሱ ፡ እደገፋለሁ
በዘለዓለም ፡ ክንዱ ፡ በእቅፉ ፡ እኖራለሁ
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
::እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
::እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
::ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist