Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Yetselot Bett Yihun lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


በልጅህ ፡ ደም ፡ "ሕይወት ፡ ሰላም ፡ ይሁን!" ፡ ብለህ
ለሐጢአታችን ፡ ይቅርታን ፡ አውጀህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ! ፡ ታረቅኸን ፡ ተመስገን
የክብርህ ፡ ማረፊያ ፡ መቅደስህ ፡ አደረግኸን ፡ መቅደስህ ፡ አደረግኸን
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
ዙፋንህ ፡ በሰማይ ፡ የሆነ ፡ ንጉሥ
በምድር ፡ በእኛ ፡ መሃል ፡ ስምህ ፡ ይቀደስ
የመዓዛ ፡ ሽታ ፡ መሥዋዕታችንን
ምሥጋናን ፡ ተቀበል ፡ከሕይወታችን ፡ ከሕይወታችን
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
ቅዱስ! ፡ ቅዱስ! ፡ ቅዱስ! ፡ እያሉ ፡ መላዕክት
በትጋት ፡ ሲያመልኩህ ፡ ቀንም ፡ ሆነ ፡ ሌሊት
ከእኛም ፡ ይድረስህ ፡ ውዳሴ ፡ ማሕሌት
ምልጃም ፡ ጸሎታችን ፣ ምሥጋና ፡ ስግደት ፣ ምሥጋና ፡ ስግደት
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
::የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
መቅረዝህም ፡ ይንደድ ፣ ይታይ ፡ ብርሃንህ
የጸሎት ፡ ቤትህን ፡ ሙላው ፡ በክብርህ
አሕዛብም ፡ ይምጡ ፡ ወደ ፡ ጸዳልህ
ይስገዱልህ ፡ ድነው ፡ በቅዱስ ፡ ስምህ በቅዱስ ፡ ስምህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
::የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የዓለም ፡ ገበያ ፡ እንዳይሆን ፡ ማትረፊያ
ቀድሰህ ፡ ጠብቀው ፡ የአንተን ፡ ማደሪያ
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ፈውስን ፡ መቀበያ
ይሁንልን ፡ ቤትህ ፡ የመንፈስ ፡ መኖሪያ፡ የመንፈስ ፡ መኖሪያ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
::የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
::የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists