Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Maderyawochih lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
::በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
::ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
::ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ
ክቡር ፡ ድንጋዮች ፡ ሕያዋን ፡ ልጆች
በበጉ ፡ ደም ፡ የተዋጁ ፡ ሰዎች
ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ለመሆን ፡ ታነጹ
ማደሪያ ፡ ሆኑለት ፡ ለንጉሡ
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
::በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
::ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
::ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ
በዓለም ፡ አዕላፍ ፡ ዕርካታን ፡ ያጡ
ዝናህን ፡ ሰምተው ፡ ከሩቅ ፡ የመጡ
በኃጥአን ፡ ድንኳን ፡ ከሚቀመጡ
በአንተ ፡ ማደሪያ ፡ መጣል ፡ መረጡ
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
::በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
::ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
::ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ
በጓዳዎችህ ፡ ክቡር ፡ ነገሮች
ተከምረዋል ፡ የሰማይ ፡ ሃብቶች
በመብራት ፡ በዘይትህም ፡ ቅባቶች
እጅግ ፡ ደመቁ ፡ የአንተ ፡ ልጆች
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
::በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
::ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
::ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ
ካህናቶችህ ፡ በመለከቶች
መዘምራን ፡ በዜማ ፡ ዕቃዎች
ባንድነት ፡ ቃና ፡ ወጣ ፡ ድምጻቸው
ከፍ ፡ አደረጉህ ፡ በምሥጋናቸው
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
::በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
::ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
::ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ
በዘለዓለማዊው ፡ ምሕረቱ
ልኡል ፡ ጐበኘን ፡ በቸርነቱ
ጌታ ፡ ለሕዝቡ ፡ ሰጠ ፡ ሞገሱን
የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ሞላ ፡ መቅደሱን
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
::በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
::ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
::ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists