Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Yetefawin Mann Yifeligal lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


ቤቱ ፡ ፈርሶ ፡ እያየህ ፡ የእግዚአብሔር
የራስህን ፡ ኑሮ ፡ ልታሳምር
ያለጌታ ፡ ልትከብር ፡ ሮጠሃል ፡ እስከዛሬ
ውስጡ ፡ ግን ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ የጨበጥከው ፡ ፍሬ
የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
::የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
::ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
::የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?
በጐቹ ፡ ለአራዊት ፡ መብል ፡ ሆኑ
እረኛ ፡ በማጣት ፡ ተበተኑ
ራስህን ፡ ስታሰማራ ፤ ለምቾትህ ፡ ስትሠራ
ይታይህ ፡ ወዳጄ ፡ የመንጋው ፡ መከራ
የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
::የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
::ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
::የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?
መክሊትህ ፡ ወዴት ፡ ነው? ወንድሜ ፡ ሆይ!
እንደ ፡ ሃኬተኛው ፡ ቀበርከው ፡ ወይ?
የሰጠህ ፡ ይጠይቅሃል! አደራውን ፡ የት ፡ አድርገሃል?
የምትጠፋውን ፡ ነፍስ ፡ ከእጅህ ፡ ይፈልጋል
የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
::የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
::ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
::የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?
ነፍስን ፡ ሊሰበስብ ፡ የተጠራ
ለጠፉት ፡ የሚያዝን ፡ የሚራራ
የምሥራች ፡ የሚያወራ
በፍጻሜው ፡ ይሸለማል
ዘለዓለም ፡ ይደምቃል ፡ እንደ ፡ ሰማይ ፡ ጸዳል
የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
::የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
::ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
::የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists