Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Eyesus Kristos lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


ሰማያት ፡ አርጅተው ፡ ከምድር ፡ ጋር ፡ ሲያልፉ
በውስጣቸው ፡ ያሉት ፡ ኃይላትም ፡ ሲጠፉ
አንተ ፡ ግን ፡ አቤቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያው ፡ ነህ
መለወጥ ፡ ሳያሻህ ፡ ደምቀህ ፡ ትኖራለህ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
::ትላንትናም ፡ ዛሬ
::እስከ ፡ ለዘለዓለም
::ያው ነህ
::ያው ነህ
::ያው ነህ
አኝ:አምናማልከው:ሳይ ታቺ:ሳይዳክም
በሥልጣኑ ፡ ገኖ ፡ ይኖራል ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ዖሜጋም ፡ ነው ፡ ጌታ
በበረቱብን ፡ ላይ ፡ ክንዱ ፡ የበረታ
::ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ
::ተጠብቀናል ፡ ታማኝ ፡ በሆነው
::ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ጉያ
ገና ፡ ኃጢአተኞች ፡ በደለኞች ፡ ሳለን
የእግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ በክርስቶስ ፡ አየን
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ ፡ የእኛን ፡ መርገም ፡ ወስዶ
ጽድቁን ፡ አልብሶናል ፡ ማቃችንን ፡ ቀዶ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
::ትላንትናም ፡ ዛሬ
::እስከ ፡ ለዘለዓለም
::ያው ነህ
::ያው ነህ
::ያው ነህ
ባኛላይ:ያለው:ካጥንቲም:ያሳብከው
ዛሬም ፡ እንዳየነው ፡ ዓላማህ ፡ ፍቅር ፡ ነው
በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ ኖረናል ፡ ተማምነን
በድል ፡ እንዘልቃለን ፡ በእጆችህ ፡ ተይዘን
::ሃሌ ፡ ሉያ ሃሌ ፡ ሉያ ሃሌ ፡ ሉያ
::ተጠብቀናል ፡ ታማኝ ፡ በሆነው
::ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ጉያ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
::ትላንትናም ፡ ዛሬ
::እስከ ፡ ለዘለዓለም
::ያው ነህ
::ያው ነህ
::ያው ነህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists