Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Ante Yemtitegna lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


የሰማይ ፡ ብርሃን ፡ ጨለማውን ፡ ገፍፎ
ሲዖል ፡ ድል ፡ ተነስቶ ፡ ሞትም ፡ ተሸንፎ
በኃጢያት ፡ ተወግተው ፡ ደክመው ፡ ለወደቁ
ጥሪው ፡ ያስተጋባል ፡ ሙታን ፡ እንዲነቁ
አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል
ማየት ፡ በሌለበት ፡ መስማት ፡ በጠፋበት
ምሬትና ፡ ፀፀት ፡ ለቅሶ ፡ ከሞላበት
ምንድን ፡ ነው ፡ የጣለህ ፡ እንደምንስ ፡ መጣህ
ከሕያዋን ፡ ምድር ፡ ፈጥነህ ፡ ለምን ፡ ወጣህ
አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል
ከእንቅልፍ ፡ የምትነሳበት ፡ ሰዓት ፡ ነው
ጊዜህን ፡ መርምረው ፡ ዘመኑን ፡ እወቀው
እንግዲያውስ ፡ ንቃ ፡ ተነስ ፡ ተመላለስ
አንተም ፡ ተመልሰህ ፡ የጠፉትን ፡ መልስ
አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል
ድፍረትህን ፡ አትጣል ፡ ብድራት ፡ አለና
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ ተነስ ፡ እንደገና
የደከመው ፡ እጅህ ፡ የዛለው ፡ ጉልበትህ
ዳግም ፡ ተጠናክሮ ፡ ያፈራል ፡ ሕይወትህ
አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists