Tesfaye Gabisso - Egziabhear Sireda lyrics
Artist:
Tesfaye Gabisso
album: Yayihal
በሕይወት ጐዳና ፈተና ቢበዛም
ጌታን እየጠራ ንጹህ ሰው አይጠፋም
እጄን ያዘኝ ብሎ ሲጮህ ይሰማዋል
ከረግረግ አውጥቶ በድል ይመራዋል
እግዚአብሔር ሲረዳ ከሰማያት ወርዶ
በደልን ሲያስወግድ በቅንነት ፈርዶ
አላያችሁም ወይ ወጥመዱ ሲሰበር
ምርኮኛው ተለቆ ማዳኑን ሲናገር
ችግረኛውን ሊውጥ ጠላት ሲገዳደር
በሚያስፈራራ ቃል በትዕቢት ሲናገር
ደርሶ የሚታደግ እግዚአብሔር ብቻ ነው
በሰው መታመን ግን የከንቱ ከንቱ ነው
እግዚአብሔር ሲረዳ ከሰማያት ወርዶ
በደልን ሲያስወግድ በቅንነት ፈርዶ
አላያችሁም ወይ ወጥመዱ ሲሰበር
ምርኮኛው ተለቆ ማዳኑን ሲናገር
ያለውን ተነጥቆ ሁሉን ነገር አጥቶ
ከአጠገቡ የሚቆም ጌታ ብቻ ቀርቶ
በእንግድነት አገር ተገፍቶ ለሚያልፈው
ተስፋው መሰረቱ አምላኩ ብቻ ነው
እግዚአብሔር ሲረዳ ከሰማያት ወርዶ
በደልን ሲያስወግድ በቅንነት ፈርዶ
አላያችሁም ወይ ወጥመዱ ሲሰበር
ምርኮኛው ተለቆ ማዳኑን ሲናገር
የቅዱሳን ረድኤት ከሰማይ ይመጣል
ዘመናትን ቆጥሮ ጌታ ይመለሳል
የልጆቹን እንባ ከዓይናቸው ያብሳል
ክብርና ምሥጋና ለሥሙ ይሆናል
እግዚአብሔር ሲረዳ ከሰማያት ወርዶ
በደልን ሲያስወግድ በቅንነት ፈርዶ
አላያችሁም ወይ ወጥመዱ ሲሰበር
ምርኮኛው ተለቆ ማዳኑን ሲናገር
እግዚአብሔር ሲረዳ ከሰማያት ወርዶ
በደልን ሲያስወግድ በቅንነት ፈርዶ
አላያችሁም ወይ ወጥመዱ ሲሰበር
ምርኮኛው ተለቆ ማዳኑን ሲናገር
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist