Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Bekristos Eyesus lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ ለልጆቹ
ይህ ፡ ነው ፡ መንገዱ ፡ ለምርጦቹ
ብድራታቸውን ፡ ያስተዋሉ
የጌታን ፡ መስቀል ፡ ይመርጣሉ
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን
እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ
ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ
እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ
በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው
የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ
ለዚች ፡ ዓለም ፡ የሚመቹ
ነውረኛውን ፡ ትርፍ ፡ ያከማቹ
በኩርነታቸውን ፡ አቃለዋል
በሥጋ ፡ ምቾት ፡ ተጠምደዋል
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን
እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ
ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ
እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ
በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው
የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ
ጌታን ፡ አክብሮ ፡ መጐስቆሉ
እንደ ፡ ጉድፍ ፡ የትም ፡ መጣሉ
የመዳን ፡ ምልክት ፡ ክብራችን
ድል ፡ መምቻችን ፡ ነው ፡ መስቀላችን
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን
እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ
ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ
እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ
በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው
የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ
ጌታን ፡ ምሰሉ ፡ በኑሮአችሁ
ከጠፊ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ አላችሁ
ውጡ ፡ ተለዩ ፡ እባካችሁ
ፍፁማን ፡ ሁኑ ፡ በልባችሁ
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን
እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ
ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ
እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ
በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው
የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists