Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Nefsae Wedamlakua lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ
ሲተጉ የሚያገኛቸው ሲመጣ ጌታቸው
በመክሊታቸው የሰሩ ምሥጋና አላቸው
አገልግሎቱን ያልናቀ በጥቂቱ ታምኖ
ብድራቱን ይቀበላል ሥራው ተፈትኖ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ
አደራው ከቶ የማይገዳቸው ቸልተኞች
የጌታቸውን መመለስ የረሱ ዝንጉዎች
ዕድላቸው ለቅሶ ነውና ዋይታ እንዳይጠብቀኝ
መንፈስህ ዘወትር ያንቃኝ ለክብርህ አቁመኝ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ
ጥቂት ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት
እንደ ሆነ መች አጣሁት ከቶ የእኔ ሕይወት
እንግዲያው ታከተኝ ሳልል ልሩጥ ለጌታዬ
የሰነፍ ሰው ሞት እንዳልሞት ልፅና በዓላማዬ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ሌት ተቀን ልስራና ስራዬን ልጨርስ
መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ አበቃሁኝ
ኃይማኖትን ጠብቄያለሁ ሩጫውን ጨረስኩኝ
እንደ ጳውሎስ ለማለት ተፈፀመ እንደ ኢየሱስ
ምሥጋናዬንም እንዳቀርብ ለሠራዊት ንጉሥ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ
ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ
ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists