Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Temesgen lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


ሥራህ ያመሰግንሃል
ቅዱሳን ያከብሩሃል
ጌትነትህም ገብቷቸው
ተንበርክኳል ጉልበታቸው
ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ኢየሱስ ተመስገን
እውነትህን ጠብቀሃል
ለተበደሉት ፈርደሃል
የተጠቃውን ታድገሃል
በማዳንህ ከፍ ብለሃል
ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ኢየሱስ ተመስገን
ደሃ አደጉን ተቀብለህ
ለተራበ ምግብን ሰጥተህ
ምጻተኛ አስጠግተሃል
ግዞተኛውን ፈተሃል
ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ኢየሱስ ተመስገን
የተቀደሰ ሥምህን
በዜማ ቅኔ ላመስግን
በአንተ ሆኖልኝ የመዳን ቀን
ስለወጣሁ ከሰቀቀን
ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን
ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ኢየሱስ ተመስገን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists