Kishore Kumar Hits

Tesfaye Gabisso - Wongel lyrics

Artist: Tesfaye Gabisso

album: Yayihal


በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን
ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ ፡ በጐ ፡ ወታደር
በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
ለተጨነቀ ፡ ልቡ ፡ እረፍት ፡ አግኝቶ
ጉዞውን ፡ ቢጀምር ፡ ወደ ፡ ሰማያዊ ፡ አገር ፡ አቅንቶ
ሰይጣን ፡ በተንኮል ፡ በወጥመዱ ፡ አጥሮ ፡ መንገድ ፡ ቢዘጋበት
ጌታም ፡ ይህን ፡ አይቶ ፡ ወጥመዱን ፡ ሰባብሮ ፡ በሩን ፡ ከፈተለት
በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን
ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ ፡ በጐ ፡ ወታደር
በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
መዋጋትን ፡ እንዲለምድ ፡ ሸለቆ ፡ ወርዶ
ከቤት ፡ ከንብረቱ ፡ ከነፍሱ ፡ አብልጦ ፡ ጌታውን ፡ ወዶ
ሰልፉ ፡ በረታና ፡ ክፉኛ ፡ ተጠቅቶ ፡ እጅና ፡ እግሩ ፡ ዝሎ
ኢየሱስ ፡ ደርሶለት ፡ ድልን ፡ አወጀለት ፡ ባላንጣውን ፡ ጥሎ
በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን
ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ ፡ በጐ ፡ ወታደር
በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
እጆቹን ፡ በእርፉ ፡ ላይ ፡ አንዴ ፡ አሳርፏል
ወደኋላ ፡ ማየት ፡ ነውር ፡ በመሆኑ ፡ ሥራውን ፡ ቀጥሏል
እምነት ፡ ሳይጓደል ፡ አደራ ፡ ሳይበላሽ ፡ ተጠንቅቆ ፡ ታግሎ
እፎይ ፡ ማለቱ ፡ ነው ፡ በክብር ፡ ተራራ ፡ አክሊል ፡ ተቀብሎ
በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን
ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ ፡ በጐውን ፡ በጐ ፡ ወታደር
በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን
ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ ፡ በጐ ፡ ወታደር
በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists