Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Alsham lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Eweraredalehu, Vol. 4


አዝ፦ አልሻም ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነገር
ምኞቴ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ማክበር
የበላይ ፡ ሆነህ ፡ በሕይወቴ
ያንግስህ ፡ መላው ፡ እኔነቴ (፪x)
ሌላውማ ፡ ሌላውማ
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ገብቶኛል ፡ ለእኔ ፡ እንደማይስማማ (፪x)
አየሁት ፡ ለእኔ ፡ እንደማይስማማ (፪x)
ዓይኔን ፡ አንስቼ ፡ ከሌላው ፡ ላይ
ሾምኩህ ፡ ጌታዬ ፡ በልቤ ፡ ላይ
ግራ ፡ ቀኝ ፡ ብልም ፡ አያምርብኝም
ያለአንተ ፡ ለእኔስ ፡ አይሆንልኝም
እርካታዬን (፫x) ፡ እርካታዬን ፡ እህ
ወግ ፡ ማዕረጌን (፫x) ፡ ወግ ፡ ማዕረጌን ፡ እህ
አዝ፦ አልሻም ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነገር
ምኞቴ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ማክበር
የበላይ ፡ ሆነህ ፡ በሕይወቴ
ያንግስህ ፡ መላው ፡ እኔነቴ (፪x)
ሌላውማ ፡ ሌላውማ
ከአንተ ፡ ውጬ ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ገብቶኛል ፡ ለእኔ ፡ እንደማይስማማ (፪x)
አየሁት ፡ ለእኔ ፡ እንደማይስማማ (፪x)
ልቤ ፡ ፅኑ ፡ ነው ፡ ተማመንኩብህ
ዘመኔን ፡ ለአንተ ፡ ይሄው ፡ ሰጠሁህ
ምራኝ ፡ ጌታዬ ፡ ወደ ፡ ወደድከው
እኔነት ፡ የለኝ ፡ ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ነው
እርካታዬን (፫x) ፡ እርካታዬን ፡ እህ
ወግ ፡ ማዕረጌን (፫x) ፡ ወግ ፡ ማዕረጌን ፡ እህ
አዝ፦ አልሻም ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነገር
ምኞቴ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ማክበር
የበላይ ፡ ሆነህ ፡ በሕይወቴ
ያንግስህ ፡ መላው ፡ እኔነቴ
ያሰብኩት ፡ ባይሆን ፡ የተመኘሁት
ሰላሜ ፡ በዛ ፡ በአንተ ፡ ያገኘሁት
አላማርርም ፡ ይሁን ፡ ያሰብከው
አላማህ ፡ ለእኔ ፡ ሁሌም ፡ በጐ ፡ ነው
እርካታዬን (፫x) ፡ እርካታዬን ፡ እህ
ወግ ፡ ማዕረጌን (፫x) ፡ ወግ ፡ ማዕረጌን ፡ እህ
አዝ፦ አልሻም ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነገር
ምኞቴ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ማክበር
የበላይ ፡ ሆነህ ፡ በሕይወቴ
ያንግስህ ፡ መላው ፡ እኔነቴ (፪x)
ሌላውማ ፡ ሌላውማ
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ገብቶኛል ፡ ለእኔ ፡ እንደማይስማማ (፪x)
አየሁት ፡ ለእኔ ፡ እንደማይስማማ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists