Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Diresilet lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Negistate Bikeyeru (Special Edition)


እልፍ ፡ ጥያቄ ፡ እልፍም ፡ ችግር
ታቅፎ ፡ የኖረ ፡ ሳያንገራግር
ችግሩን ፡ ቻል ፡ አድርጎ
ጌታ ፡ ይበልጣል ፡ ብሎ
ሲያመልክ ፡ ባደባባይ
ይሰማ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ይታይ
አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ
ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ
ድረስለት ፡ ለእንዲህ ፡ ዓይነቱ ፡ ሰው (፪x)
ባዶውን ፡ እንዲሁ ፡ አትመልሰው (፪x)
ሲማፀን ፡ በቆመበት ፡ ስፍራ (፪x)
አለሁ ፡ በለው ፡ ስምህን ፡ ሲጠራ (፪x)
አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ
ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ
ከወገኖቹ ፡ ከሀገር ፡ እርቆ
በባእድ ፡ ምድር ፡ ሚኖር ፡ ተሳቆ
ያሰበው ፡ ባይሞላለት ፡ ሲያለቅስ ፡ በያለበት
ራራ ፡ ስማው ፡ አቤቱ
አለሁ ፡ በል ፡ ለእንዲህ ፡ ዓይነቱ
አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ
ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ
ድረስለት ፡ ለእንዲህ ፡ አይነቱ ፡ ሰው (፪x)
ባዶውን ፡ እንዲሁ ፡ አትመልሰው (፪x)
ሲማፀን ፡ በቆመበት ፡ ስፍራ (፪x)
አለሁ ፡ በለው ፡ ስምህን ፡ ሲጠራ (፪x)
አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ
ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists