Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Yadinal lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Negistate Bikeyeru (Special Edition)


ጌታ ፡ ነው ፡ ቢጎድልም ፡ ቢሞላ
በሕይወቴ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ
ችግሩ ፡ ከቦ ፡ ቢያስጨንቀኝ
ከርስቴ ፡ ማን ፡ ሊነቀንቀኝ
እኔ ፡ አለሁ (፪x)
አልነሳም ፡ ከመሰዊያው (፪x)
ጌታ ፡ ነው ፡ ቢጎድልም ፡ ቢሞላ
በህይወቴ ፡ የለም ፡ ከሱ ፡ ሌላ
ችግሩ ፡ ከቦ ፡ ቢያስጨንቀኝ
ከርስቴ ፡ ማን ፡ ሊነቀንቀኝ
እኔ ፡ አለሁ (፪x)
አልነሳም ፡ ከመሰዊያው (፪x)
እየተፀለየ ፡ እየተዘመረ
ከቀደመው ፡ ይልቅ ፡ ችግሩ ፡ ጨመረ
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢሆን ፡ ጨምሮ ፡ ጨምሮ
እግዚአብሔር ፡ ያድናል ፡ ችግርን ፡ ሰባባሮ
እየተፀለየ ፡ እየተዘመረ
ከቀደመው ፡ ይልቅ ፡ እሳቱ ፡ ጨመረ
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢነድ ፡ ጨምሮ ፡ ጨምሮ
እግዚአብሔር ፡ ያድናል ፡ የእሳትን ፡ ኃይል ፡ ሰብሮ
ለጌታ ፡ ምን ፡ ይሳነዋል
ሕያው ፡ ነው ፡ አልተለወጠም
ያድናል ፡ ለዘላለም (፪x)
የሰጠ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ
ቢነሳ ፡ ከልካይስ ፡ አለው ፡ ወይ
አትበይ ፡ እንደሰነፎች
ከሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የሚመች
እኔ ፡ አለሁ (፪x)
አልነሳም ፡ ከመሰዊያው (፪x)
እንዲህ ፡ ነው ፡ አይባል ፡ የጌታ ፡ አሰራሩ (፪x)
ፈፅሞ ፡ አይታማም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ (፪x)
ቢዘገይም ፡ እንኳን ፡ በጊዜው ፡ ይደርሳል (፪x)
ካለቀሰ ፡ ሁሉ ፡ እንባ ፡ ይታበሳል (፪x)
ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያድናል
ለጌታ ፡ ምን ፡ ይሳነዋል
ሕያው ፡ ነው ፡ አልተለወጠም
ያድናል ፡ ለዘላለም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists