Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Nigesiligne lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Negistate Bikeyeru (Special Edition)


እግዚአብሔርን ፡ በመተማመን ፡ ተግተው ፡ የሚጠባባቁ (፪x)
ከመልካም ፡ ነገር ፡ አይጎድሉም ፡ በመከራ ፡ ቀን ፡ አይወድቁ (፪x)
ለደካሞችም ፡ ኃይላቸው ፡ ነውና ፡ እንደሚለው ፡ ቃሉ (፪x)
የረዳችሁ ፡ ያገዛችሁ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ክበር ፡ በሉ (፪x)
አዝ፦ ክበርልኝ (፪x)
በአንተ ፡ ነውና ፡ ያማረብኝ
ንገስልኝ (፪x)
በአንተ ፡ ነውና ፡ ሰው ፡ የሆንኩኝ
ክበር ፡ ክበርልኝ (፪x)
ንገስ ፡ ንገስልኝ (፪x)
ቆይቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት ፡ እሱም ፡ ዘንበል ፡ አለልኛ (፪x)
ታምኜው ፡ አላሳፈረኝ ፡ ጌታ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ (፪x)
ጠብቆ ፡ ያልከሰረ ፡ የወጣ ፡ ከጭንቅ ፡ ከማጡ (፪x)
ያክብረው ፡ በዝማሬ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ክብርን ፡ ያምጡ (፪x)
አዝ፦ ክበርልኝ (፪x)
በአንተ ፡ ነውና ፡ ያማረብኝ
ንገስልኝ (፪x)
በአንተ ፡ ነውና ፡ ሰው ፡ የሆንኩኝ
ክበር ፡ ክበርልኝ (፪x)
ንገስ ፡ ንገስልኝ
ንገስ ፡ ንገስልኝ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists