Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Maeregu lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Negistate Bikeyeru (Special Edition)


ዝም ፡ ቢል ፡ አንደበት ፡ እጆችም ፡ ባይዘረጉ
አይቀንስ ፡ ችሎታው ፡ አይቀንስ ፡ ማዕረጉ
የሰማይ ፡ ቅዱሳን ፡ ደግሞም ፡ መላዕክቱ
ሁሌ ፡ ይቀኙለታል ፡ ላፍታም ፡ ሳይታክቱ
ካፅናፍ ፡ እስካፅናፍ ፡ ተርፏል ፡ የሚያመልከው
የፍቅሬን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ እርሱ ፡ ምን ፡ ሊጎድለው
የዳንኩ ፡ እኔ ፡ ያመለጥኩ ፡ እኔ
ተፈወስኩ ፡ እኔ ፡ የሞተው ፡ ለእኔ
እቀኛለሁኝ ፡ ለመድህኔ (፪x)
እዘምራለሁ ፡ ለመድህኔ (፪x)
ቢወደድ ፡ አይበዛ
ቢፈቀር ፡ አይበዛ
ክበር ፡ ቢባል ፡ አይበዛ
ቢመሰገን ፡ አይበዛ
ነፍሴን ፡ ከሞት ፡ ስለገዛ
ክበር ፡ ቢባል ፡ ከቶ ፡ አይበዛ
ነፍሴን ፡ ከሞት ፡ ስለገዛ
ክበር ፡ ቢባል ፡ ከቶ ፡ አይበዛ
አከብርሀለሁ (፬x)
እወድሀለሁ (፬x)
እንካ ፡ ተቀበለው ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው
እንካ ፡ ተቀበለው ፡ ዝማሬየም ፡ ይኸው
እንካ ፡ ተቀበለው ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው
እንካ ፡ ተቀበለው ፡ መጓደዴም ፡ ይኸው
ዝም ፡ ቢል ፡ አንደበት ፡ እጆችም ፡ ባይዘረጉ
አይቀንስ ፡ ችሎታው ፡ አይቀንስ ፡ ማዕረጉ
የሰማይ ፡ ቅዱሳን ፡ ደግሞም ፡ መላዕክቱ
ሁሌ ፡ ይቀኙለታል ፡ ላፍታም ፡ ሳይታክቱ
ካፅናፍ ፡ እስካፅናፍ ፡ ተርፏል ፡ የሚያመልከው
የፍቅሬን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ እሱ ፡ ምን ፡ ሊጎድለው
የዳንኩ ፡ እኔ ፡ ያመለጥኩ ፡ እኔ
ተፈወስኩ ፡ እኔ ፡ የሞተው ፡ ለእኔ
እቀኛለሁኝ ፡ ለመድህኔ (፪x)
እዘምራለሁ ፡ ለመድህኔ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists