Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Kurat Kurat Alegne lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Eyesus Eyalefe Newe


ምርጡ ተብሎ ታምኖበት
ልብን በእሱ ላይ ተጥሎ
አለልኝ ለኔ እያለ መኖር ሲመኝ ተዘልሎ
የተደገፈው ሸምበቆ መሆኑን እንዲያው ሳያውቀው
ድንገት ተሰብሮ ወደቀ የዛ ሠው መተማመኛው
እኔማ በላዬ ላይ ንጉሴን ሾምያለሁ
አልፈራ አልደነግጥ በክንዱ እኮራለሁ
እኔ ግን በላዬላይ ንጉሴን ሾምያለሁ
አልፈራ አልደነግጥ በክንዱ እኮራለሁ
ኩራት ኩራት አለኝ ብኮራስ ምን አለ
እመካለሁ እኔስ እመካብሀለሁ
አንበሳው እየሱስ የኔ ሆኖ የለ
ሀይለኛው እየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ
ሀይለኛው እየሱስ የኔ ሆኖ የለ
ወዳጄ እየሱስ ቤቴን ሞልቶት የልለ
እንዳንተ ያለ ከቶ የለምና
በሰማይ በምድር አልተገኘምና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
አይኔ አረፈብህ ወዳጄ በምንም የማትረታ
ወረት አታውቅም እንደ ሠው በጎ ነው ሁሌ የኔ ጌታ
ዘመናት ሲፈራረቁ አልተቀየረም መውደድህ
ሁሉን በእጆችህ ይዘሀል ታስመካለህስ ቢመኩብህ
በልቤ ሾሜሀለሁ ከፍ ብለህ ደምቀህ ታይ
እንዳንተ የለምና በምድር በሠማይ
በልቤ ሾሜሀለሁ ከፍ ብለህ ደምቀህ ታይ
እንዳንተ የለምና በምድር በሠማይ
ኩራት ኩራት አለኝ ብኮራስ ምን አለ
እመካለሁ እኔስ እመካብሀለሁ
አንበሳው እየሱስ የኔ ሆኖ የለ
ወዳጄ እየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ
ሀይለኛው እየሱስ የኔ ሆኖ የለ
ወዳጄ እየሱስ ቤቴን ሞልቶት የልለ
እንዳንተ ያለ ከቶ የለምና
በሰማይ በምድር አልተገኘምና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
በመከራ ቀን ቢጠሩት አለሁ የሚል ሞልቶ
ግራ ለገባው መጠጊያ ሚደግፍ እጁን ዘርግቶ
መተማመኛው ጌታ ነው ተፈትኖ አልፏል በብዙ
ደጋግ እጆቹን አይተናል ደካማዎቹን ሲያግዙ
አለልኝ የኔጌታ የማይጥል የማይከዳ
ሰባራን የሚጠግን ወዳጅ ነው በምድረ በዳ
አለልኝ የኔጌታ የማይጥል የማይከዳ
ሰባራን የሚጠግን ወዳጅ ነው በምድረ በዳ
ኩራት ኩራት አለኝ ብኮራስ ምን አለ
እመካለሁ እኔስ እመካብሀለሁ
አንበሳው እየሱስ የኔ ሆኖ የለ
ወዳጄ እየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ
ሀይለኛው እየሱስ የኔ ሆኖ የለ
ወዳጄ እየሱስ ቤቴን ሞልቶት የልለ
እንዳንተ ያለ ከቶ የለምና
በሰማይ በምድር አልተገኘምና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና
ይብዛልህ ዛሬም ምስጋና
ይብዛልህ ነገም ምስጋና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists