Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Betezega Bete lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Deg Neh , Vol. 5


በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል
ሰላም ይሁን ለኔ ብለሃል
ችግሬን የረሳሁብህ
ልነሳ እስኪ ላምልክህ
በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል
ሰላምህን ለኔ ሰጥተሃል
ችግሬን የረሳሁብህ
ልነሳ እስኪ ላምልክህ

ኮቴ ሳይሰማ በር ሳይንኳኳ
ከቤቴ የገባህ ጌታ አንተ ነህ ለካ
የታል ያ እጅህ ስለኔ የደማው
ቁስሌ የሻረበት መገኛዬ እሱ ነው
በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል
ሰላም ይሁን ለኔ ብለሃል
ችግሬን የረሳሁብህ
ልነሳ እስኪ ላምልክህ
በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል
ሰላምህን ለኔ ሰጥተሃል
ችግሬን የረሳሁብህ
ልነሳ እስኪ ላምልክህ

በር ዘግተን አዝነን ተቀምጠን
እንዳይገደሉን አይሁዶችን ፈርተን
ውሎ አደረ ልብ እንደዋለለ
'ምንጠብቀው ጌታ ወዴት አለ
ከመከራ የሚያግዝ ሲታጣ
ቢጨላልም ቀን እስከሚወጣ
ከተፍ ሲል ባልጠበቅነው ሰዓት
ተወገደ መጨነቅ መባባት
የሰላሜ ምንጭ አንተ ሰላሜ ሆይ
ለአፍታ አትለይ 'ባክህ ከቤቴ ቆይ (ጌታ)
መገኘትህን አትውሰድብኝ
ጥጋቤ አንተው ነህ ሌላው ሁሉ ይቅርብኝ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ሰላሜ ሆይ
ለአፍታ አትለይ 'ባክህ ከቤቴ ቆይ
መገኘትህን አትውሰድብኝ
ጥጋቤ አንተው ነህ ሌላው ሁሉ ይቅርብኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists