Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Deg Neh lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Deg Neh , Vol. 5


እንዲህ ያለ መውደድ ከቃላት ያለፈ
ስለጠላቶቹ ነፍሱን ያሳለፈ
ፍጥረት በሙሉ ተደንቆ ዋለ
ፍቅር እንደ አንተ የለም እያለ
ፀሀይም አለች ብርሃን ለምኔ
መስቀል ላይ ሲውል ደጉ መድኔ
ባህሪህ ባህሪህ
ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ
ባህሪህ ባህሪህ
ቢያስገርመኝ ደግ ነህ አልኩህ

ወደ ሞት ሲነዳ - ደግ ነህ የአዳም ዘር በሙሉ - ደግ ነህ
ሞቱን ሞተህለት - ደግ ነህ ደርሰሃል ለሁሉ - ደግ ነህ
ነፍስን እስከመስጠት - ደግ ነህ ፍቅር ተፈትኖ - ደግ ነህ
ከፍርድ አመለጠ - ደግ ነህ ሁሉ በአንተ ሆኖ - ደግ ነህ
ባህሪህ ባህሪህ
ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ
ባህሪህ ባህሪህ
ቢያስገርመኝ ደግ ነህ አልኩህ

ለጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ከተገኘ
ሀጥእ ተስፋ ቆርጦ መኖር ባልተመኘ
ግን ተገለጠ ፍቅር ለሁሉ
አመለጡብህ ጌታ ነህ ያሉ
ለየት ያለ ነው ያንተስ ፍቅር
መሰከሩልህ ሰማይ ምድር
ባህሪህ ባህሪህ
ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ
ባህሪህ ባህሪህ
ቢያስገርኝ ደግ ነህ አልኩህ

አቅም አጥተህ አይደል ተሸንፈህ
በጨካኞች ጡጫ ላይ መውደቅህ
እንደሚታረድ በግ እየነዱ
በመስቀል ሊገድሉህ ወደዱ
አቅም አጥተህ አይደል ተሸንፈህ
በጨካኞች ጡጫ ላይ መውደቅህ
እንደሚታረድ በግ እየነዱ
በመስቀል ሊገድሉህ ወደዱ
ባህሪህ ባህሪህ
ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ
ባህሪህ ባህሪህ
ቢያስገርመኝ ደግ ነህ አልኩህ

አወይ አጨካከን ጠፍቶ የሚራራ
እያወካከቡ ነዱት በተራራ
አፉ አልተከፈተ ክፉ አልተናገረ
ጭራሽ ለሚጠሉት ይማልድ ጀመረ
ወዶ ዓለም ቢያወድሰው
በርግጥ ስለሚገባው ነው
ለኛ ብሎ ታርዷልና
ለሱ ይገባል ምስጋና
ወዶ ዓለም ቢያወድሰው
በርግጥ ስለሚገባው ነው
ለኛ ብሎ ታርዷልና
ለሱ ይገባል ምስጋና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists