Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Yetawokilegne lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Deg Neh , Vol. 5


በሰፊው ጎዳና ትውልድ ሲተራመስ
የልቡ ላይሞላ ያሰበበት ላይደርስ
በቀጭኑ መንገድ ጌታን ብቻ ይዞ
ወደ እረፍት ይገባል ተጉዞ ተጉዞ ተጉዞ ተጉዞ
በሰፊው ጎዳና ትውልድ ሲተራመስ
የልቡ ላይሞላ ያሰበበት ላይደርስ
በቀጭኑ መንገድ ጌታን ብቻ ይዞ
ከጽዮን ይደርሳል ተጉዞ ተጉዞ ተጉዞ ተጉዞ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
ምርጫዬ ጌታ ነው እኔም የሱ ነኝ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
ምርጫዬ ጌታ ነው እኔም የሱ ነኝ
የሱ ነኝ የሱ ነኝ
የሞት መውጊያ አያሰጋኝ
የሱ ነኝ የሱ ነኝ
ሲዖል ገሀነም አያስፈራኝ

ግርግር ቢበዛ ግፊያ በመንገዱ
ጠቢባን ነን ባዮች ወደዛ ቢነጉዱ
የምህረቱ ደጃፍ ድንገት ሳይዘጋ
ኢየሱስን ብሎ ማምለጥ አለው ዋጋ ማምለጥ አለው ዋጋ
ግርግር ቢበዛ ግፊያ በመንገዱ
ጠቢባን ነን ባዮች ወደዛ ቢነጉዱ
የምህረቱ ደጃፍ ድንገት ሳይዘጋ
ኢየሱስን ይዞ ማምለጥ አለው ዋጋ ማምለጥ አለው ዋጋ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
ምርጫዬ ጌታ ነው እኔም የሱ ነኝ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
ምርጫዬ ጌታ ነው እኔም የሱ ነኝ
የሱ ነኝ የሱ ነኝ
የሞት መውጊያ አያሰጋኝ
የሱ ነኝ የሱ ነኝ
ሲዖል ገሀነም አያስፈራኝ
ዕድል ፋንታዬ እግዚአብሔር ነው
የኔ ጠበቃ ኢየሱስ ነው
ዕድል ፋንታዬ እግዚአብሔር ነው
የኔ አማላጅ ኢየሱስ ነው
የሱ ነኝ የሱ ነኝ
የሞት መውጊያ አያሰጋኝ
የሱ ነኝ የሱ ነኝ
ሲዖል ገሀነም አያስፈራኝ
የሱ ነኝ የሱ ነኝ
የሞት መውጊያ አያሰጋኝ
የሱ ነኝ የሱ ነኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists